Get Mystery Box with random crypto!

የኡጋንዳ የልዑካን ቡድን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስ | Ethiopian Artificial Intelligence Institute

የኡጋንዳ የልዑካን ቡድን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ

የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም እንዲሁም የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጀነራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደህንነትና ወታደራዊ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና እና ከፍተኛ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡

ቡድኑ በነበረው ቆይታ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ኢንስቲትዩቱ እያካሄደ ስለሚገኘው ዘርፈ ብዙ ክንውኖች በዋና ዳይሬክተሩ አማካኝነት ገለጻ ተደርጎለታል፡፡