Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን #በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትም | Ethiopian Students

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን #በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ #ጥቅምት_01 ቀን እና #ጥቅምት_02 ቀን 2012 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣
ብርድልብስና አንሶላ፣
የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
የስፖርት ትጥቅ

በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://
portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ተማሪዎች ከወላጆቻቸውና በአካባቢያቸው ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር ውል ተፈራርመው የማረጋገጫ ወረቀት ካላመጡ ዩኒቨርስቲው የማይቀበል መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል፡፡
በተጨማሪም ባለፈው ስርዓተ ትምህርት መሠረት በመጀመሪያ ዓመት 1ኛ እና 2ኛ ሴሚስተር በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች ከዘድሮ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡እንዲሁም መደበኛ የድህረ ምረቃ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 06 2012 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Via አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa