Get Mystery Box with random crypto!

አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም በዐቢይ ዜማ አ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ፤ በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ፤ እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ፤ በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ ነው።

ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ "አቡነ ዘበሰማያት" ይስጥ። እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርያላይሶን ይበል። ሕዝቡም እንደርሱ ይበሉ።

ከዚህ በኋላ በቅኔ ማኅሌት ሁሉም ይሰብሰቡ። መቋሚያ ይዘው በመካከላቸው ጧፍ አብርተው ይያዙ። የዳዊትንና የነቢያትንም ጸሎት እየተቀባበሉ ያንብቡ። አንብበው ሲጨርሱ በመካከላቸው ያለውን መብራት በያዙት መቋሚያ ያጥፉት። የዲያቢሎስ ገዢነት መደምሰስ ምሳሌ ነው። ከዚያም መዘምራን ንሴብሖን ይዘምሩ። ካህናትም ሕዝቡን በወይራ ቅጠል እየጠበጠቡ እና ስግደት እየሰጡ ወደ ቤታቸው ይሸኟቸው።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox