Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘአርብ ስቅለት አርብ ጠዋት በ፲፪ ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘአርብ ስቅለት

አርብ ጠዋት በ፲፪ ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም፤ ርግዘተ ገቦሁ ነአምን፤ ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን፤ ዬ ዬ ዬ፤ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ።

በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ምስባክ
መዝ: ፳፮ ፣ ፲፪
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፤
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ፤
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ:-

ማቴ: ፳፯ : ፩ - ፲፬ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል።

ማር: ፲፭ : ፩ - ፭ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።

ሉቃ: ፳፪ : ፷፮ - ፸፩ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ።

ዮሐ: ፲፰ : ፳፰ - ፵ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን "መልክዐ ሕማማት" ያድርሱ።

አርብ ጠዋት በ፫ ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪)፤ ይስቅልዎ ሖረ፤ ዬ ዬ ዬ፤ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ።

በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል። በቀመጠል ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ:-

ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ፤
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ፤
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ።

ይ.ዲ ምስባክ:- መዝ: ፳፩ : ፲፮
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤
ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።

ማቴ: ፳፯ : ፲፭ - ፲፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።

ማር: ፲፭ : ፮ - ፲፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ።

ሉቃ: ፳፫ : ፲፫ - ፳፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን።

ዮሐ: ፲፱ : ፩ - ፲፪ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክዓ ሕማማት ያድርሱ።

አርብ በስድስት ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫)፤ ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ።

በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል። ከዚያም ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-

ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤
ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ፤
ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ወኆለቊ ኲሎ አዕፅምትየ
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:-

ማቴ: ፳፯ : ፳፯ - ፵፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ።

ማር: ፲፭ : ፲፮ - ፴፫ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ።

ሉቃ: ፳፫ : ፳፯ - ፵፬ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን።

ዮሐ: ፲፱ : ፲፫ - ፳፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ።

አርብ በዘጠኝ ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ፤ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል። ከዚያም በኃላ ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-

ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል። በመቀጠልም ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ፤ ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ)። አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ። እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቁጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ። ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:-

አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:-

ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ፤ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ።
ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ፤
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:-

ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ።

ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ።

ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክዐ ሕማማት ያድርሱ።

አርብ በአስራ አንድ ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም፤ ዬ ዬ ዬ፤ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ፤ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ።

በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" የለም።

ሥርዓተ እግዚኦታ
ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዓተ ግንዘትን ይስሩ። ሦስት ካህናትም ሥርዓተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት። አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል። አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት በመያዝ ፊት ለፊት ይምራ። በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ። ከዚህ በኋላ በአራቱም ማዕዘናት እየዞሩ እግዚኦታ ያድርሱ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox