Get Mystery Box with random crypto!

ለመሆኑ እብኖዲ፣ ትስቡጣ ፣ ማስያስ ፣ ታኦስ ፣ ናይናን እና ኪርያላይሶን ትርጉማቸው ምንድን ነው? | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ለመሆኑ እብኖዲ፣ ትስቡጣ ፣ ማስያስ ፣ ታኦስ ፣ ናይናን እና ኪርያላይሶን ትርጉማቸው ምንድን ነው???

@Ethiopian_Orthodox

በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዚእነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡ ፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው።
ታኦስ-የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ-የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው።
ትስቡጣ-«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።
አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ – ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው።
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ-የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

@Ethiopian_Orthodox

የ፵፩ ስግደት ምን እየተባለ ይሰገዳል?
አንድ ክርስቲያን በጾም ጊዜ ከጸሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ ፵፩ ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ:-
፲፪ ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
፲፪ ጊዜ በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
፲፪ ጊዜ ኪርያላይሶን
፭ ጊዜ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ(አምስቱ የጌታ ችንካሮች)
እነዚህም ቢደመሩ ፵፩ ይሆናሉ፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox