Get Mystery Box with random crypto!

12. በሀገራችን በልዩ ልዩ ቦታዎች የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያናችን ከመሠረቱ ችግ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

12. በሀገራችን በልዩ ልዩ ቦታዎች የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያናችን ከመሠረቱ ችግሩ እንዳይፈጠር ለማድረግ የሰላም ጥሪ ማቅረቧ፣ ችግሩም ከተፈጠረ በኋላ ሰብዓዊ ድጋፍን ስታደርግና ስታስተባብር መቆየቷ፣ በዋናነትም ችግሩ እንዲፈታ ሕዝቡን በማስተማር የሰላም ጥሪ በማቅረብ መግለጫዎችን በማውጣት፣ ጾምና ጸሎት እንዲያዝ በማድረግ ያበረከተችው አስተዋጽዖ እውቅና እንዲያገኝ ጉባኤው እየጠየቀ በቀጣይም በሰብዓዊ ድጋፍም ሆነ በጸሎት ሕዝቡን በማስተማርና ወደአንድነት እንዲመጣ በማድረግ በየጊዜው የሰላም ጥሪ በማስተላለፍ ቀጣይነት ያለው ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው አሳስቧል፡፡
13. ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ስር በሚገኙ መምሪዎች እና ድርጅቶች ለመልካም የሥራ ውጤት የተደረገውን ጥረት ጉባኤው በደስታ ተቀብሎታል፡፡ በመሆኑም ለበለጠ የሥራ ውጤት በመልካም አስተዳደር እየታገዙ አስፈላጊውን ክትትል እየተደረገ ሥራቸውን አሻሽለው እንዲቀጥሉ ጉባኤው አሳስቧል፡፡
14. ቤተ ክርስቲያን በጎቿን የምታሰማራበት መንፈሳዊ መሣሪያ ሁለገብ ትምህርት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጨለማው ዓለም ብርሃን እንድትሆን የመሠረታት ናት፡፡ የቤተ ክርስቲያን መኖር ደግሞ የምእመናን የመኖር ነጸብራቅ በመሆኑ ምእመናንን በቃለ እግዚአብሔር አንጾና በሚፈለገው መልኩ ቀርጾ ማውጣት የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም በአባቶቻችን ለዚሁ ዓላማ ታስቦ የተከፈቱ ሁሉም መንፈሳዊ ኮሌጆች የሰባኪያንና የዘመናዊያን ምሁራን መፍለቂ ምንጮች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች መገኛዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ከየኮሌጆቹ የሚመረቁ ደቀ መዛሙርት በየተመደቡበት አህጉረ ስብከት እየተገኙ የተጣለባቸውን አደራ በተገቢው መንገድ እንዲወጡ፣ ኮሌጆቹን የቅበላ አቅማቸውን ከፍ አድርገው በብቃትና በጥራት በማስተማር ተመራቂዎችን እንዲያበዙ ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ቃል እንገባለን፡፡
ቀደም ሲል ከነበሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቂት መንፈሳውያን ኮሌጆች በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ የተከፈቱ አዳዲስ ኮሌጆች መኖራቸው ጉባኤው መሠረታዊ ጉዳይ አድርጎ ወስዶታል፡፡ በመሆኑ ኮሌጆቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሂደትን እንዲያስቀጥሉ፣ የችግሮች መፍትሔ እንዲሆኑና በዕቅድና ጥናት ላይ ተመሥርተው የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲያፋጥኑ ጉባኤው አሳስቧል፡፡
በየአህጉረ ስብከቱ ጽ/ቤቶችና መንፈሳዊ ኮሌጆች እየተሰጡ ያሉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች መልካም ጅምር በመሆናቸው ጉባኤው አድናቆቱን እየገለጸ ቀጣይ ሂደቱ ግን የቤተ ክርስቲያኒቱን አቅም ባገናዘበ ሃብትን በጠበቀና በዕቅድ ላይ በተመሠረተ እንዲሆን ጉባኤው አሳስቧል፡፡
15. ለቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ ተልእኮ መሳካት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ልማት ላይ በማተኮር እየተደረገ ያለውን ጥረት በማጠናከር እና ቤተ ክርስቲያናችን በገቢ ራሷን ማስቻል እንዳለብን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ ሆኖም በቤተ ክርስቲያኒቱ እየተከናወነ ያለውን የአዳዲስ ሕንጻ ግንባታ አስመልክቶ ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ካገኘነው ግንዛቤ ከፍተኛ መሻሻል እንዳለ ተገንዝበናል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ የተጀመሩ ሕንጻዎች የሚጠናቀቁበት፣ አዳዲስ ሥራዎች የሚጀመሩበት ሂደት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲቀጥል ጉባኤው እያሳሰበ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ቤተ ክርስቲያን አስተማማኝ የገቢ አቅም እንዲኖራት የበኩላችንን አስተዋጽዖ እናደርጋለን፡፡
16. የሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ ከውጭ ሀገር በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ እስከ አሁን ድረስ ከ45 ሺህ በላይ ሕጻናትን ያሳደገ መሆኑን ጠቅሶ አሁን ግን እርዳታው በመቆሙ ሕጻናት የማሳደግ ኃላፊነቱን ለመወጣት አለመቻሉ የተገለጸ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ወላጆቻቸውን ያጡና ድጋፍና እንክብካቤ የሚፈልጉ ሕጻናት ቁጥር በጥናት እንደተረጋገጠው ከ4 ሚሊየን በላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ስለዚህ የድርጅቱ ጠንካራ እና ደካማ ጎን በሚገባ ተፈትሾ ኃላፊነቱን በሚገባ ይወጣ ዘንድ አስፈላጊው ድጋፍና መመሪያ እንዲሰጠው እንዲሁም አህጉረ ስብከት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል ባሳለፈው መሠረት በየአካባቢያቸው የሚገኙ ሕጻናት ማሳደጊዎች አድባራትና ገዳማትን፣ ካህናትና ምእመናንን በማስተባበር ችግረኞች ሕጻናትን እንዲያሳድጉ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

በጉባኤው እነዚህና ሌሎች የአቋም መግለጫዎች ተነበዋል፡፡

EOTCMK

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox