Get Mystery Box with random crypto!

ጥር አርፋ በነሐሴ ወር ሁለት ሱባኤ ይዘው ሲጨርሱ በነሐሴ 14 መልአኩ ቅዱስ ሥጋዋን ከገነት አምጥ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥር አርፋ በነሐሴ ወር ሁለት ሱባኤ ይዘው ሲጨርሱ በነሐሴ 14 መልአኩ ቅዱስ ሥጋዋን ከገነት አምጥቶ ሰጥቷቸው በጸሎትና በምሕላ ቀብረዋታል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም፡፡ በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ተነሥታ ስታርግ፣ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፡፡ በዚህ ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው፣ ለእርሱ የቀረበት መስሎት አዝኖ ‹‹በፊት የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ፤ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ ከደመናው ለመውደቅ ተመኘ፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አጽናናችው፡፡ ከእርሱ በቀር ትንሣኤዋን ሌላ እንዳላየ ነገራው ለምስክር እንዲሆነው ሰበኗን/መግነዝ ሰጥታው ዐረገች፡፡

ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ ክብርት እናቱ እመቤታችም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጇ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋ ‹‹እንደ ልጅዋ ትንሣኤ›› ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡

ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት፡፡ እርሱም ምስጢሩን ደብቆ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› አላቸው፡፡ ሐዋርያትም ‹‹አንተ ተጠራጣሪ ነህ›› ብለው መቃብሩን ሊያሳዩት ሲከፍቱ አጧት፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹እመቤታችን ተነሥታ አርጋለች›› ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው፡፡ ‹‹ለምስክር ይሁንህ›› ብላ የሰጠቸውንም ሰበኗን አሳያቸው፡፡ ሐዋርያትም ይህን አይተው ትንሣኤዋን አመኑ። ሰበኗን ቆራርጠው ለበረከት ተከፋፍለው ወደየሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል፡፡ ዛሬም በመጾር መስቀልና በካህናት እጅ መስቀላቸው ላይ የሚያስሯት ‹‹መሀረብ›› የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡ በዓመቱም ሐዋርያት ‹‹ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን!›› ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በነሐሴ 16 ቀንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አሳርጎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቅዳሴ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም የመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገቷን በዓይናቸው አይተውና በሚገባ ተረድተው ዓለምን ዙረው አስተምረዋል፡፡

በድጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለኃጥአን ሁሉ እጅግ እያዘነች ኖረችና አምላካችን ተወዳጅ ልጇ የሰጣትን ዘላለማዊ የድኅነት ቃልኪዳን ባሰብን ነፍሳችን ሀሴት ታደርጋለች፡፡ ቃልኪዳኗንም ዘወትር በማሰብ እንጽናናለን፡፡ ክብርት እመቤታችን አምላካችንን ተወዳጅ ልጇን "... በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው፡፡ ከአንተ ጋራ የደረሰብኝን ረኀቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ›› አለችው፡፡ ተወዳጅ ልጇ መድኃኔዓለም ክርስቶስም ‹‹ወላጅ እናቴ ሆይ! እንዳልሽው እንደወደድሽ ይሁንልሽ፡፡ ጣፋጭቱ ከመዓር ከሸንኮር የሚጥመው ንጹሕነቱ ከኤዶም ምንጭ ውኃ ንጣቱ ከበረዶና ከወተት የበለጠውን ወተት መግበው ባሳደጉኝ ጡቶችሽ ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ትእዛዜንና ሕጌን ባስተማሩ ዓስራ አምስቱ ነብያት፣ ሄሮድስ ባስገደላቸው ዓስራ አራት እልፍ የቤተልሔም ሕፃናት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ የወንጌልን መንግሥት ለዓለም በሰበኩ ሐዋርያት፣ ስለእኔ ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፈው ስለሰጡ ሰባ ሁለቱ አርድእት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ዙፋኔ በተዘጋጀባት ሉዓላዊት ሰማይ፣ የእግሬ መረገጫ በሆነች ታህታዊት ምድር ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ነደ እሳት በሆነ የእሳት ነጋረጃዬ ፍጹም ማደሪያዬ በሆነ በአርያም ሰማይ ቃል ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በተሰቀልኩበት ዕፀ መስቀል፣ እጅና እግሬ በተቸነከረበት ቅኖት ችንካር፣ በጦር በተወጋው ጎኔ ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በዕለተ ዓርብ በፈሰሰው ደሜ በሕመሜና በሞቴ፣ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊትም በከርሰ መቃብር ባደርኩበት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ከመቃብር ወጥቼ አዳምን ከነልጆቹ ከሲኦል ለማውጣት ወደሲኦል በመውረዴ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ሙስናን መቃብርን አጥፍቼ በመነሳቴ፣ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጌ ዳግመኛም ዓለምን ለማሳለፍ በታላቅ ምስጋና በምመጣበት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ክቡር በሆነ ደሜ ቅዱስ በሆነ ሥጋዬ ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ብርክት እናቴ ድንግል ማርያም ሆይ! የሰጠሁሽም ቃልኪዳን እንዳይታበል አማንዬ ብዬ በራሴ ማልኩልሽ›› አላት፡፡
~~~~~~~~
እናቱን ለሁላችን ለምንታመንባት እናታችን አድርጎ ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን፣ በምልጃዋ ይማረን፡፡
~~~~~~~~

በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox