Get Mystery Box with random crypto!

የነሐሴ ፲፫ ግጻዌ + መልእክታት ዘቅዳሴ:- 1. ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፳፫ - ፴ 2. ፪ኛ ጴ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የነሐሴ ፲፫ ግጻዌ

+ መልእክታት ዘቅዳሴ:-
1. ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፳፫ - ፴
2. ፪ኛ ጴጥሮስ ፩ : ፲፭ -ፍጻሜ
3. ግብረ ሐዋርያት ፯ : ፵፬ - ፶፩

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ።
መዝራእትከ ምስለ ኃይል።
ትርጉም፦
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል።
ስምህንም ያመሰግናሉ።
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤
(መዝ ፹፰ : ፲፪ - ፲፫/88:12-13)

+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፱ : ፳፰ - ፴፰ /9:28-38
፳፰
ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
፳፱
ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
፴፩
በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
፴፪
ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
፴፫
ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
፴፬
ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
፴፭
ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
፴፮
ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ። ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
፴፯
በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ / ዘዲዮስቆሮስ {በዕዝል ዜማ}

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox