Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ ‹‹በምጽዓት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መን | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ ‹‹በምጽዓት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም›› የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው ነበረ፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡ ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚሸነፍ ስላወቀ ‹‹ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ›› የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡

ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በወኅኒ ቤት እያለ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ እየመጡ ያጽናኑት ነበር፡፡ ‹‹ውዳሴ ሐዋርያት›› የተሰኘውንና ከሐምሌ 5 ጀምሮ በ12ቱም ወራት የሚመሰገኑበት የሐዋርያትን ምስጋና የያዘውን መጽሐፍ ያዘጋጀው በወኅኒ ቤት ሆኖ ጴጥሮስና ጳውሎስ ከጎበኙት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ በእስር ላይ ሳሉ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት መሞታቸው ተሰማ፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ያሳሰረህ ንጉሥ ሞቷል›› በማለት ነገሩት፡፡ ይህንንም ተቻኩለው የነገሩት ያሰረው ንጉሥ መሞቱን ሲሰማ ይደሰታል ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኖ የሰጣቸው መልስ ‹‹አይ ንጉሡ ባይሞት እኔም እንደታሰርኩ ብቀር ይሻል ነበር፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትኮ እኔን ባይወደኝ የአምላክን እናት እመቤታችንን ይወዳት ነበር›› አላቸው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ አባ ጊዮርጊስን ከወኅኒ ቤት አውጥቶት በጥንቱ ቦታ አስቀመጠው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን የቤተ መንግሥትን ነገር ለመሸሽ ስለ ፈለገ በጋሥጫ ከመቀመጥ ይልቅ ርቆ ጥንት ወደ ነበረበት ወደ ዳሞት በመሄድ ማስተማር ጀመረ፡፡ ወደ ዳሞት ሲሄድ እግረ መንገዱን ወደ ደብረ ሊባኖስ ገብቶ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር ተሳልሟል፡፡ በዚያ ጊዜ የደብረ ሊባኖሱ አበ ምኔት እጨጌ ዮሐንስ ከማ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ነበሩ፡፡ አባ ጊዮርጊስን በዕውቀቱ የሚቀኑበት፣ በችሎታው የሚመቀኙት ሰዎች ነገር ሠርተው ከንጉሥ ቴዎድሮስ ጋር ስላጣሉት እልም ካለ በረሃ እንዲጋዝ ተደረገ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ከግዞት የወጣው ዐፄ ቴዎድሮስ ሲሞት ነበር፡፡

የአባ ጊዮርጊስ ሌላው ተማሪ የነበረው ዐፄ ይስሐቅ በ1399 ዓ.ም መንግሥቱን ሲይዝ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት አውጥቶ ወደ ጋሥጫ መለሰው፡፡ በዚያ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ እድሜው 42 ዓመት ሲሆን በስደትና በጤንነት መታወክ የተነሣ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜውን በጾም፣ በጸሎትና በድርሰት ያውለው ነበር፡፡ አንድ ቀን ቴዎድሮስ የተባለ መስፍን፣ ዳግመኛም የጦሩ አዛዥ የሚሆን፣ አባ ጊዮርጊስን ስለ ርትዕት ሃይማኖት በጠየቀው ጊዜ አባ ጊዮርጊስም ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ሰጠው፡፡ ንጉሡና የምሥጢር ሊቃውንት የሆኑ ካህናት ይህንን በተመለከቱና ባነበቡ ጊዜ ‹‹በእውነት ዮሐንስ አፈወርቅና አፈ በረከት የሆነው ቄርሎስ በዘመናችን ተነሥተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ቍስጥንጥንያን መስላለች፣ ከእስክንድርያም በላይ ከፍ ከፍ ብላለች›› ብለው አደነቁ፡፡ ይህም ፍካሬ ሃይማኖት የተሰኘው ድንቅ ድርሰቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውንና የምታወግዘውን በግልጽና በዝርዝር የጻፈበት መጽሐፍ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በፍካሬ ሃይማኖት ድርሰቱ ላይ የዘረዘራቸው የመናፍቃን ስሞችንና ክህደታቸውን ስንምለከት በዘመኑ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያላቸውን ዕውቀት በግልጽ ያሳየናል፡፡ አባ ጊዮርጊስ መከራ ያልተለየው አባት በመሆኑ አሁንም በቤተ መንግሥት የነበሩ ሰዎች የእርሱን መከበርና መወደድ አይፈልጉትም ነበር፡፡ በተለይም ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› የተሰኘውን መጽሐፍ በመጻፉ በዚህም ዝናው የበለጠ ስለተነገረ እነርሱ በሁሉም ዘንድ መከበሩን አልወደዱትም ነበር፡፡ ስለዚህም ነገር ሠርተው ከዐፄ ይስሐቅ ጋር አሁንም አጣሉት፡፡

ዐፄ ይስሐቅ አባ ጊዮርጊስን አሳስሮ ውኃ ወደማይገኝበት ዓለታማ ቦታ አጋዘው፡፡ በዚያም በመከራ ለብዙ ጊዜ ኖረ፡፡ በዚያ እያለ ዘወትር በጸሎት አብዝቶ ይተጋ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ዐፄ ይስሐቅ ወደ ልቡናው እንዲመለስ አደረገ፡፡ ንጉሡ በአባ ጊዮርጊስ ላይ የፈጸመው ነገር ሁሉ ስለፀፀተው አገልጋዮቹን ጠርቶ አባ ጊዮርጊስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ ነገር ግን እነዚያ ተንኮል ሠሪዎች የአባ ጊዮርጊስ መምጣት ተንኮላቸውን ስለሚያጋልጠው ‹‹አባ ጊዮርጊስ ሞቷል›› ብለው አስወሩ፡፡ ይህንን ሲሰማ ዐፄ ይስሐቅ ፈጽሞ አዘነ፡፡ አባ ጊዮርጊስም ሞቷል እየተባለ መወራቱን ከደቀ መዝሙሩ ስለ ሰማ በሕይወት የመኖሩን ዜና ጽፎ ለዐፄ ይስሐቅ እንዲያደርስለት መልእክቱን በአውሎ ንፋስ አሳስሮ ላከለት፡፡ አውሎ ንፋሱ ለአባ ጊዮርጊስ በመታዘዝ ደብዳቤውን ተሸክሞ በመሄድ ዐፄ ይስሐቅ በድንኳን ተቀምጦ በነበረ ጊዜ ጉልበቱ ላይ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡ ምትሐት የተሠራበት ስለመሰለው ደነገጠና መኳንንቱንና ሕዝቡን ሰብስቦ ጉዳዩን ገለጠ፡፡ ወዲያውም ነፋሱ ያመጣለትን መልእክት እሳት አስነድዶ ከዚያ ውስጥ ቢጥለው ሊቃጠል አልቻለም፡፡ ወደ ውኃም ቢጨምረው አልጠፋም፡፡ በዚህ ተደንቆ ወረቀቱን ከፍቶ አነበበው፡፡ ደብዳቤው ከአባ ጊዮርጊስ የተላከ መሆኑን ሲያውቅ ዐፄ ይስሐቅ ደነገጠ፡፡ እነዚያን መልእክተኞች ይዞ ወደ ወኅኒ ከጨመራቸው በኋላ አባ ጊዮርጊስን ከግዞት ያወጡት ዘንድ ላከ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲመጣ ንጉሡ በደስታ ተቀብሎ ማረኝ ብሎ ለመነው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይቅር አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብዳቤውን በማን እጅ እንደ ላከው ጠየቀው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ደብዳቤውን በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ በነፋስ እንደ ላከው አስረዳው፡፡
ከግዞት ከተመለሰ በኋላ እመቤታችን ተገልጣለት መከራው ሁሉ እንደ ሐዋርያት መሆኑን ገለጠችለት፡፡ አእምሮውን ብሩህ፣ ልቡናውን ትጉኅ የሚያደርግ እጅግ ብዙ ምሥጢርም ነገረችው፡፡ ተሰናብታው ከሄደች በኋላ ‹‹እጅግ ብዙ መብራት አቅርቡ አምስት ፈጣን ጸሐፊዎችንም አምጡ›› ብሎ አዘዘ፡፡ ከዚህም በኋላ እርሱ እየነገራቸው እነርሱ እየጻፉ እረፍት ሳያደርጉ ሦስት ቀን ሙሉ አጽፎ ‹‹መጽሐፈ ምሥጢር›› የተሰኘውን መጽሐፍ ፈጸመ፡፡ አምስቱ ጸሐፍትም የየድርሻቸውን አጠናቅቀው በአንድ አደረጉት፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይህን ተመልክቶ በእጅጉ አደነቀ፡፡ ‹‹እኔ የዚህን መጽሐፍ ቃል አልተናገርኩም፤ መንፈስ ቅዱስ በእኔ አፍ ተናገረ እንጂ›› ሲል በወቅቱ መስክሯል፡፡ የመጽሐፉንም ስም ‹‹መጽሐፈ ምሥጢር›› ብሎ የሰየመው ራሱ ነው፡፡ የጻፈው በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም የዚህ መጽሐፍ