Get Mystery Box with random crypto!

በኳተር ከሙስሊም ኮሚኒቲ ጋር ውይይት ያደረገው የጠቅላይ ም/ቤ ልዑካን ቡድን ለተጠየቀው ጥያቂ | "ኡማ ቲቪ " Tv

በኳተር ከሙስሊም ኮሚኒቲ ጋር ውይይት ያደረገው የጠቅላይ ም/ቤ ልዑካን ቡድን ለተጠየቀው ጥያቂ ምላሽ ሰጠ

ግንቦት /3/2015

የሒጃብ ጉዳይ በጉራጌ ክልል በጉንችሬ ከተማ ሰለተነሳው ጥሰት ጠቅላይ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሂጃብ የተፈጠረው ችግር እንደተቀረፈው ሁሉ የጉንችሬውም ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴርን ህግ ክልከላውን ለማስነሳት ከሚመለከተው አካል ከዚያም ከፍ ብሎ ካሉ አካላት ጋር ኡስታዞቻችን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ኡስታዝ አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ያሉበት ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራበት መሆኑ ተገልጿል ።

የሙስሊሞቸ ቀልብ ማረፊያ የሆነው እና የአላህ ቤት መስጅዶች እየፈረሰ በመሆኑ የተነሳ ጥያቄን

ይህ ጉዳይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ትልቅ ሥራው ነው ።በወቅቱ የኦሮሚያ መጅሊስ ችግር ነበረበት ያንን ችግር ቀርፈን አግዘናቸው በተዋረድ አሰራር ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገርን ነው ብለዋል ።

በኳታር የመጅሊስ ቅርጫፍ አንዲከፈትም ለተጠየቀው የኮሚኒቲ ጥያቄ

ይህ የአብሮነት አበረታች ጥያቄን ጉዳዩ በምሁራን እያጠኑት እንደህነ ውጭ ያሉ ሙስሊሞች ከዚህ መጅሊስ እንዴት ይጠቀሙ የሚለውን ኮሚቴው ጥናቱን ከጨረሰ ኢንሻ አላህ ተጠያቂነቱ ለእኛ የሚሆን መጅሊስ ይኖራችኋል ብለው ቃል ገብተውላቸዋል።

በውጪ አገር የምንኖር ሙስሊም ወገኖቻቹህ በማህበራዊ ኑሯችን ውስጥ 'የኒካህ ሰርተፍኬት' ለማግኘት የቃዲ ችግረ አለብን።
ይህ ማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚኖር መጋባትና ፍቺም በተባለው አቅጣጭ መፍትሄ አንደሚፈለግ ተገልጿል።

-በሰኮላር ሽፕ ዙሪያ ያነሷቸው ችግር የተሰጠው ማብራሪያ

የሸሪዓ ትምህርት ማግኘት ይችላሉ የሚል ሲሆን ሌላው አውቃፍ ተደርጎ ኢማሞችና ኡስታዞች ቀጣይነት ያለው እርዳታ ተደርጎ የዳዕዋ ስራን ማስቀጠል ይቻላል

የኢትዮጵያ አስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑካን ከኮማኔቱ ጋር መደፊት ተቀራርበው እንደሚሰሩ ይህ የጋራ ተቋማቸውን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።