Get Mystery Box with random crypto!

ሳዑዲ ውስጥ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የመንገድ ላይ ፍተሻ በአደንዛዥ ዕፅ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው | "ኡማ ቲቪ " Tv

ሳዑዲ ውስጥ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የመንገድ ላይ ፍተሻ በአደንዛዥ ዕፅ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፤ አደንዛዥ ዕፅ ሲባል ጫትንም ያጠቃልላል፤ እንዲሁም መኪና ውስጥ መሳርያ፣ ስለት እና ዱላ አስቀምጦ መገኘት ያስጠይቃል... ፍተሻው ከተለመደው መልኩ ጠበቅ ያለ ስለሆነ ኢቃማችሁ የተበላሸ (ህጋዊ ያልሆናችሁ) ሰዎች ጥንቃቄ ብታደርጉ መልካም ነው... ትራፊኮችም ክላውዶ (ፈህስ አደውሪ) እያዩ ነውና ያልታደሰ የቆየ ከሆነ ማደስ... ተፍቲሽ (ፍተሻ) ውስጥ ስንገባ ኢስባት ስንጠየቅ (መንጃ ፍቃድ መታወቅያ ሊብሬ) ያለምንም መደናገጥ መስጠት ... አደንዛዥ ዕፅ ባታጨስም ሚጨስበት ቦታ ላይ መገኘት በእራሱ ያስጠይቃል... ጥያቄ እንዳይበዛ ብዙ ገንዘብ በካሽ ይዞ አለመንቀሳቀስም መልካም ነው... በተረፈ አማን ነውና እንዳትፈሩ እንዳትሸበሩ