Get Mystery Box with random crypto!

የአላህ ድንቅ ጥበብ «እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡» [አ-ስ'ሶፋት: 06] | "ኡማ ቲቪ " Tv

የአላህ ድንቅ ጥበብ

«እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡»
[አ-ስ'ሶፋት: 06]

የሰው ልጆች እውቀት ውስን ነው:: በዚህ በተሰጠው ውስን እውቀት የፍጥረተ አለሙን ግኝቶች ለመመራመር ብዙ ጥረት ያደርጋል::

ከዚህ ጥረቶች መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካው የህዋ ምርምር ተቋም ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመሆን 10ቢሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በ30አመታት ውስጥ የገነባው ጀምስ ዌብ የተሰኘው ግዙፉ ቴሌስኮፕ ከምድር አንድ ሚሊዮን በላይ ማይሎች ርቆ ካለበት የላካቸው የጥልቁ ህዋ ምስሎች አለምን እያስደመሙ ይገኛሉ::

ምስሎቹ እጅግ ውብ እና አስደማሚ ናቸው:: በሰው ልጆች እውቀት የሚሰሩ የቅንብር ምስሎች እንኳን ይህን ያህል አያስገርሙም::

የጠፈር ተመራማሪዎች እነዚህን ውብ እና ግዙፍ ፍጥረታት መኖራቸውን አውቀው እንዴት እንደተፈጠሩ ጥቂት እውቀት ቢያገኙም ማን እንደፈጠራቸው ግን አንድ ታላቅ ሃይል አለ ከማለት ውጪ ፈጣሪያቸው አላህ መሆኑን ለማመን ያንገራግራሉ::

አላህ (ሱ.ወ) መሰል ተዓምራቶቹን አስመልክቶ ይህን ይለናል

سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ ۗ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

،،እርሱም(ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን?,, (ፉሲለት 53)

ምስሎቹን በተመለከት የሚከተሉትን የጌታችን ቃል እናስተንትን

إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ)
«እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡»
[አ-ስ'ሶፋት: 06]

تَبَارَكَ الَّذِي جَعَلَ فِي السَّمَاءِ بُرُوجًا وَجَعَلَ فِيهَا سِرَاجًا وَقَمَرًا مُّنِيرًا)
«ያ በሰማይ ቡሩጆች(ትላልቅ ኮከቦች)ን ያደረገና በእርሷም ውስጥ አንጸባራቂ(ፀሐይ)ንና አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ፡፡»

ጌታችን አላህ ጥራት ይገባው::

ሱብሐን አሏህ
ustaz Abubeker Ahmed