Get Mystery Box with random crypto!

ንግድ ባንክ በግማሽ አመቱ 13 ቢሊየን ብር አተረፈ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ አመቱ የ10 | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ንግድ ባንክ በግማሽ አመቱ 13 ቢሊየን ብር አተረፈ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ አመቱ የ102.4 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ገለፀ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ6ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርቧል። በዚህም የባንኩ የግማሽ አመት ትርፍ 13 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጿል።

ባንኩ የተደራሽነት እና የአገልግሎት ተደራሽነትን መሰረት በማድረግ ሲሰራ መቆየቱን ያነሱት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቤ ሳኖ በዚህም በግማሽ አመቱ 55 አዳዲስ ቅርንጫፎችንና 99 ATM ማሽኖችን በተለያዩ አካባቢዎች ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል። ባንኩ የአገልግሎት አድማስን ከማስፋት በዘለለ ለስራ እድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሰራው ስራም አጠቃላይ የሰራተኛውን ቁጥር ወደ 39ሺህ ከፍ ማድረጉን እንዲሁ ያስታወቀ ሲሆን በተለይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው ለሚወጡ አዳዲስ ስራ ፈላጊዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰርቷል ነው የተባለው።

የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በሚመለከትም የእቅዱን 111 በመቶ ማሳካቱና ለገቢ ንግድና ሌሎች የውጭ ምንዛሬ ለሚያስፈልጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች 3.9 ቢሊዮን ዶላር ማቅረቡ ተመላክቷል። የደንበኞቹን የሂሳብ ደህንነት ከመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ የጥንቃቄ እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከኤጀንቶች ጋር በሰራው ስራም የአገልግሎት ተደራሽነት አድማስን ማስፋት እና የደንበኞችን አገልግሎት ማሟሟላት መቻሉ ተመላክቷል፡፡

እንደ አጠቃላይ በግማሽ አመቱ የባንኩ ጠቅላላ ሃብት 1.2 ትሪሊየን ብር መድረሱም እንዲሁ ተገልጿል፡፡