Get Mystery Box with random crypto!

የሕወሓት ታጣቂዎች በኮረምና አላማጣ አካባቢ ስጋት ፈጥረዋል ተባለ ሐሙስ ጥር 25 ቀን 2015 ( | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የሕወሓት ታጣቂዎች በኮረምና አላማጣ አካባቢ ስጋት ፈጥረዋል ተባለ

ሐሙስ ጥር 25 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የማይጨው አካባቢዎች የሚገኙ የሕወሓት ታጣቂዎች የሚነዙት ፕሮፖጋንዳ በኮረምና አላማጣ አካባቢዎች ትልቅ ስጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡

ታጣቂዎቹ ከኮረም 40 ኪሎሜትር ገደማ እርቀት ላይ በማይጨው የሚገኙ ሲሆን፤ በየጊዜው ኮረምና አላማጣ እንገባለን የሚሉ ዛቻዎችን እየሰነዘሩ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

በዚህም ነዋሪዎቹ ትልቅ ስጋት እንዳደረባቸው ገልጸው፣ አሁንም ከስድስት ያላነሱ ቀበሌዎች በህወሓት ቁጥጥር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀበሌዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎች ገንዝብ እንዲሁም ቀለብ አምጡ በሚሉ የህወሓት ታጣቂዎች በደል ውስጥ መሆናቸውንም ከእነዚህ አካባቢዎች ወደ ኮረም ለገበያ ከሚመጡ ሰዎች አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

በጦርነቱ ወቅት ከኮረምና ለአለማጣ ወደ ትግራይ ሄደው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች አሁን ላይ ብዙዎቹ ወደ ቦታቸው እየተመለሱ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፣ ነገር ግን ከተመለሱ በኋላ የተወሰኑት ለህወሓት ታጣቂዎች መረጃ በማድረስና በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ ከመቀሌ ወደ ኮረም የተላከን እርዳታ ቁሳቁስ፣ ማህበረሰቡ እኛ እየተዳደርን ያለነው በአማራ ክልል ስለሆነ በትግራይ ክልል በኩል የሚመጣን እርዳታ አንቀበልም በማለት የመጣውን መልሶ መላኩን ተናግረዋል፡፡

መሰል ድርጊቶችም የማህበረሰቡን የደህንነት ስጋት ከፍ እንዲል አድርጎታል ነው ያሉት፡፡

በትናንትናው ዕለት ከቆቦ ወደ አላማጣ የሚወስደው መንገድ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለዚህም አንዱ ምክንያት ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ የአማራ ተወላጆች በትግራይ ክልል ባሉ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ በመሆኑ ወደክልሉ የሚያልፍ ነገር መኖር የለበት በሚል እንደሆነነ ተመላክቷል፡፡

የትግራይ ታጣቂዎች በጦነቱ ወቅት ከአማራ ክልል የወሰዷቸውን በርካታ ሰዎች በየእስር ቤቶች አጉረው እያሰቃዩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በዚህም ማይጨው ላይ ብቻ 250 የአማራ ተወላጆች ታስረው የሚገኙ ሲሆን፣ ሶረም ወረዳ ውስጥ ደግሞ ቁጥራቸው የማይታወቅ ብዙ ሰዎች በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ አክለዋል፡፡