Get Mystery Box with random crypto!

ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋ | ESAT International

ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

ሀሰተኛ የኢትዮጵያን የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ ከነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች መካከል ዮሴፍ ተከስተብርሃን እና ተክለብርሃን ገ/መስቀል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታቋል፡፡

ግለሰቦቹ በቡድን በመደራጀት ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን አትመው ሲያሰራጩ መቆየታቸውን የጠቆመው ፖሊስ ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በተደረገባቸው ጥብቅ ክትትልና ድንገተኛ ፍተሻ 40 ሺህ ሃሰተኛ ባለ አንድ መቶ ብር የገንዘብ ኖቶች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር ያልዋለውና የቡድኑ አባል የሆነው ሶስተኛው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ እንደነበረው በፖሊስ ምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ግለሰቡ ለጊዜው ቢሰወርም በደህንነትና በጸጥታ አካላት ክትትል ስር መሆኑን ከፖሊስ ኮሚሽኑየተገኘው አመልክቷል፡፡

@ethiomereja1 ሼር