Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ሱዳንን አስጠነቀቀች። በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ጆን ጎድፍሬይ ፤ ካርቱም ሩሲያ በቀይ | 🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

አሜሪካ ሱዳንን አስጠነቀቀች።

በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ጆን ጎድፍሬይ ፤ ካርቱም ሩሲያ በቀይ ባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር እንድትመሰርት ከፈቀደች ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው አስጠንቅቀዋል።

ከ25 ዓመታት በኋላ በሱዳን የመጀመርያው የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ጎድፍሬይ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ሱዳንን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መነጠል ብቻ ሳይሆን ጥቅሟን የሚጎዳ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

አምባሳደር ጎድፍሬይ ከሱዳን አል ታይያር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤ "ሩሲያ በቀይ ባህር ላይ የጦር ሰፈር ለመመስረት እ.ኤ.አ. በ2017 ከስልጣን ከተወገዱት ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው የሚሉ አንዳንድ ሪፖርቶች አሉ"  ብለዋል።

አልበሽር ለወራት የዘለቀን ተቃውሞ ተከትሎ ከስልጣን የተወገዱት በሚያዝያ 2019 እንደነበር ይታወቃል።

የአሜሪካው ዲፕሎማት " የሱዳን መንግስት የጦር ሰፈሩ (የሩስያ) እንዲቋቋም እንዲቀጥል ከወሰነ ወይም እንደገና ለመደራደር ከወሰነ ለሱዳን ጥቅም ጎጂ ነው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ሁሉም አገሮች ከየትኞቹ አገሮች ጋር አጋር እንደሚሆኑ የመወሰን ሉዓላዊ መብት አላቸው " ያሉት አምባሳደሩ " ነገር ግን እነዚህ ምርጫዎች በእርግጥም መዘዝ አላቸው " ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ አሜሪካ በሱዳን አዲስ በሲቪል የሚመራ መንግስት እና ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና የሚመልስ የሽግግር ማእቀፍ ለማየት ትፈልጋለች።

እ.ኤ.አ ህዳር 2017 ሱዳን እና ሩሲያ በወታደራዊ ስልጠና፣ የልምድ ልውውጥ እና የጦር መርከቦችን ወደ ሁለቱ ሀገራት ወደቦች ለማስገባት የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Sudan-Tribune-09-29

ምንጭ፦ ሱዳን ትሪቢዩን

https://t.me/ethiomereja0