Get Mystery Box with random crypto!

#ጋምቤላ የጋምቤላ ክልል መንግስት የኢሰመኮን ሪፖርት 'ለጠላት የወገነ ነው ' ሲል ገልጾ ሪፖርቱ | 🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

#ጋምቤላ

የጋምቤላ ክልል መንግስት የኢሰመኮን ሪፖርት "ለጠላት የወገነ ነው " ሲል ገልጾ ሪፖርቱን እንደማይቀበለውና እንደሚያወግዘው ገለፀ።

የጋምቤላ ክልል፤ "ኢሰመኮ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ላይ ተፈጥሮ በነበረው ውጊያ ተከትሎ በክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሽያ እና ተባባሪ ወጣቶችን ሲመሩ የነበሩ አመራሮች አማካይነት ደረሰ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ያወጣውን ሚዛናዊነት የጎደለውና የአንድ ክልል የፀጥታ ተቋምን ከተራ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪ ጋር በአንድነት ያየ" ነው ሲል ገልጿል።

ሪፖርቱ "ከሁሉ በላይ በክልልና በአገር ላይ ይደርስ የነበረ ከፍተኛ ጥቃት በመቀልበስ ሂደት የህይወት መስዋዕትነት የከፈለውን የፀጥታ ተቋማችንን በጅምላ የፈረጀና የተገኘውንም ድል በዜሮ ያባዛ ሆኖ አግኝቶታል" ብሏል።

በዚህም የጋምቤላ ክልል መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት እንደማይቀበለውና አጥብቆ እንደሚያወግዘው ገልጿል።

አክሎም "የክልሉ መንግሥት ምንም እንኳን አንድም የዜጋ ህይወት እንዲጠፋ የሚፈቅድ ባይሆንም በጥፋት ቡድኖቹ በተከፈተብን ጥቃት ከንፁሃን ዜጎች እንዲሁም የፀጥታ አካላት ህይወት መጥፋት ጋር ተያይዞ ኮምሽኑ ያወጣው የምርመራ ሪፖርት ግኝት እጅግ የተጋነነ እና በወቅቱ መሬት የነበረውን ጥሬ ሀቅ ያላገናዘበ" ነው ብሏል።

"የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋምቤላ ከተማ ውስጥና ኦነግ ሸኔና ጋነግ የፈፀሙት ወረራና ጥቃት ብዥታ ተፈጥሮ የክልሉን መንግሥት እና ህዝብ በወቅቱ የተደረገውን ተጋድሎና ለዚህም የተከፈለውን መስዋዕትነት በዜሮ ያባዛ፤ ከሁሉ በላይ የክልሉን የፀጥታ ኃይል ሞራል የሚያዳክም፤ ፀረ-ሠላም ኃይሉንና መንግሥትን በአንድ ሚዛን ላይ አድርጎ ያየ በአጠቃላይ ለጠላት የወገነ ሪፖርት ሆኖ አግኝተነዋል" ሲል አሳውቋል።
https://t.me/ethiomereja0