Get Mystery Box with random crypto!

═════════════════ ልጆች መቼ ነው አልጋ ላይ መሽናት የሚያቆሙት? ═════════════ | የጤና መረጃ

═════════════════
ልጆች መቼ ነው አልጋ ላይ መሽናት የሚያቆሙት?
═════════════════
አብዛኞቹ ህፃናት 5 ዓመት ሲሆናቸው ሌሊት ላይ ሽንታቸውን መቆጣጠር ይችላሉ:: ሆኖም 10-15% የሚሆኑ ህፃናት እስከ 7 አመታቸው ድረስ ይቸገራሉ፡፡ ሽንት ለሊት ሊያመልጣቸው ይችላል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት እድሜያቸው በ 1 ዓመት በጨመረ ቁጥር ቺግሩ በ15% እየቀነሰ ይሄድና እድሜያቸው 15 ዓመት ሲሞላ 99 በመቶ ህፃናት ከዚህ አይነቱ ችግር ሙሉ ለሙሉ ነፃ ይሆናሉ፡፡
::
ሆኖም አንድ ሕጻን 6 አመት እና ከዛ በላይ ሆኖ ሽንትን ለመቆጣጠር ካልቻለ ወላጆች ሐኪም መማከር አለባቸው፡፡ ሽንትን መቆጠጠር ያለመቻል ችግር በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ላይ ከሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊና ማሕበራዊ ተፅዕኖ ይልቅ በልጆች ላይ የሚፈጥረዉ ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እጅግ የበረታ ነው፡፡
ወላጆች ሊያወቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ልጆች ሆነ ብለው አሰበውና አቅደው ወይም በእነርሱ ግድ የለሽነትና ሥንፍና የሚመጣ ችግር እንዳልሆነ ልረዱ ይገባል፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት ቺግር ያለባቸውን ህፃናት ማሸማቀቅ ማናደድ እንዲሁም በሰዉ ፊት ʺለሊት አልጋ ላይ ሸንቷል!ʺ ብሎ ማሳፈር በፍፁም ተገቢ አይደለም፡፡

ሽንትን ሌሊት ያለመቆጣጠር ችግር መንስኤው ምንድነው? ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የምከተሉት ናቸው
═════════════════
1. ትልቅ የሆነ እንቅልፍ እና የሽንት ፊኛ ከመጠን በላይ ሲወጠር መንቃት አለመቻል
2. የጉሮሮ መጥበብ እና ትንፋሽ መቆራረጥ እና ማንኮራፋት (obstructive sleep apnea)
3. በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ(በተለይ እናት እና አባት ላይ በ ልጅነታ ቸው አጋጥሞቸው ከሆነ)
4. የሆርሞን መዛባት በተለይ የቫሶፕሬሲን (ADH) የሚባለው ሆርምን ማታ ላይ በአግባቡ የማይመረት ከሆነ
5. የሽንት ፊኛ ተገቢውን የሽንት መጠን መያዝ ወይም መሸከም አለመቻል(በነርቭ ቺግር ወይም የአፈጣጠር ችግር ምክንያት)
6. የአይምሮ ጭንቀት
7. አስቸጋሪና አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ እና ያን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት
8. አሰቃቂ አካላዊ ድብደባና ቅጣት
ወሲባዊ ጥቃት/የአስገድዶ መደፈር በተለይ ሴት ታዳጊዎች ላይ
10. የነርቭ ዘንግ(spinal cord) ችግሮች(spina bifida)
11. ከፍተኛ የሺንት መጠን ማምረት - polyuria (በስኳር ፣ በኩላሊት ችግሮች ወይም በሌሎች ምክንያቶች)
12. ረጅም ጊዜ የቆየ ሆድ ድርቀት
13. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

═════════════════
ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕፃናት ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር)
═════════════════
Via:- SPMMC.
═════════════════
https://t.me/ethiomedhealth