Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ሴት ልጅ መካንነት ማወቅ ያለብን ነጥቦች። ═════════════════ ≈≈≈≈≈≈≈≈ ክፍል ① | የጤና መረጃ

ስለ ሴት ልጅ መካንነት ማወቅ ያለብን ነጥቦች።
═════════════════
≈≈≈≈≈≈≈≈ ክፍል ①≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
እርግዝና አልከሰት ብሎሻል?
እነዚህን 20 ነጥቦች አስተውይ?
═════════════════
1. የወር አበባዬ በሰአቱ ይመጣል ወይ? ( ቀኑን ጠብቆ፣ መጠኑን ጠብቆ፣ ከመጣ 3- 5 ቀን የሚቆይ)
═════════════════
2. መከላከያ ተጠቅሜ አውቃለሁ ወይ? የትኛውን ነው? መቼ ነው ያቆምኩት?
═════════════════
3. በቂ እና ጊዜውን የጠበቀ ግንኙነት አለኝ ወይ?
═════════════════
4. እድሜዬ ከ40 በላይ ነው ወይ?
═════════════════
5. ከዚህ በፊት ከማህፀን የሚወጣ ሽታ ያለው ያልታከምኩት ፈሳሽ አለ ወይ ?ወይንም የማህፀን ኢንፌክሽን ተብዬ ታክሜ አውቃለሁ ወይ?
═════════════════
6. ከዚህ በፊት በሀኪም የተነገረኝ የማህፀን እጢ አለ ወይ?
═════════════════
7. በማህፀን አካባቢ እና ሽንጤ አካባቢ ለብዙ ጊዜ የቆየ ህመም አለኝ ወይ ወይንም ደግሞ በግንኙነት ጊዜ ከባድ ህመም አለኝ ወይ?
═════════════════
8. ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ውርጃ አጋጥሞኝ ያውቃል ወይ?
═════════════════
9. ከጡቶቼ የሚፈስ ወተት የመሰለ ፈሳሽ አለ ወይ?
═════════════════
10. በጣም መሞቅ(ሙቀት ባልሆነ ጊዜ)፣ ቶሎ ባልተለመደ እና በማያበሳጭ ነገር መነጫነጭ ፣ እና አንገት ላይ የወጣ እንቅርት አለ ወይ?
═════════════════
11. ከዚህ በፊት ካንሰር ተብዬ በመድሀኒት ወይም በጨረር ታክሜ አውቃለሁ ወይ?
═════════════════
12. ከመጠን ያለፈ በሰውነት ላይ የሚወጣ ብጉር ፣ የፀጉር መሳሳት ከፍተኛ የሆነ መነቃቀል ወይም መመለጥ እና በሰውነቴ ላይ መብቀል በሌለበት ቦታ ፀጉር መብቀል አለ ወይ( የወንድ ፂም ማብቀያ ቦታ ላይ፣ በደረት ላይ እና በላይኛው የጀርባዬ ክፍል ላይ)?
═════════════════
13. ከዚህ በፊት ኦፕራሲዬን (operation) ለሆድ ችግር ወይም ለማህፀንና ፅንስ ጉዳይ አድርጌ አውቃለሁ ወይ?
═════════════════
14. ከዚህ በፊት ለውርጃም ይሁን ለከፍተኛ የደም መፍሰስ ሀኪም ቤት ገብቼ በመሳሪያ ማህፀኔ ተጠርጎልኝ ያውቃል ወይ?
═════════════════
15. አመጋገቤ እንዴት ነው? በጣም ከመጠን ያለፈ ኪሎ መቀነስ ወይም መጨመር አለኝ ወይ?
═════════════════
16. ከባለቤቴ ጋር በግንኙነት ወቅት ችግር ወይም አለመጣጣም አለ ወይ(ባንቺም ይሁን በእርሱ በኩል)?
═════════════════
17. በሀኪም የተነገረኝ በማህፀን አካባቢ ያለ የአፈጣጠር ችግር አለ ወይ?
═════════════════
18. በሙያዬ(በስራዬ) በስፖርት ላይ የተሰማራሁ እና ከባድ እንቅስቃሴ የማደርግ አትሌት ነኝ ወይ?
═════════════════
19. ደባል ሱሶች ያሉብኝ በተለይ ደግሞ ሲጋራ የማጨስ፣ አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት፣ እና አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ ሰው ነኝ ወይ?
═════════════════
20. በህይወቴ ውስጥ በስራም ጉዳይ ይሁን በቤት ውስጥ የኑሮ አለመመቻቸትና ከፍተኛ ጭንቀት አለብኝ ወይ?
═════════════════
ስለዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ አንቺን የሚመለከትሽ ካለ እና እርግዝና አልከሰት ካለሽ :- የማህፀን ሀኪምሽ በማማከር ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይኖርብሻል።

የደም ፣ የአልትራሳውንድ (Ultrasound)፣ የማህፀን ራጅ (HSG) እና ለእርግዝና እና ለወር አበባ የሚጠቅሙ የሰውነት ንጥረ ፈሳሽ መጠን(Hormone level) ምርመራ በየደረጃው ይደረጋሉ።

በነኚህ ከላይ በተጠቀሱት ምርመራዎች ላይ ችግር ካለ በየችግሩ መጠንና ሁኔታ የተለያዩ ህክምናዎች( ከመድሀኒት እስከ ቀዶ ጥገና) የተለያዩ ዘመኑ ባመጣቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዘ ህክምናው ሊደረግ ይችላል።

═════════════════
ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት
═════════════════