Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እና ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ : የ12ኛ ክፍል ብሔራ | Ethio Matric

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እና ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ :

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ፦
- ብሔራዊ ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ድረሰ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።
- የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡
- ለፈተናው የተመዘገቡት 503,812 የሶሻል ሳይንስ እንዲሁም 365,954 የናቹራል ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

የሬሜዲያል ፈተና ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ሰኔ 30/ 2015 ዓ/ም ተጠናቋል።
- አሁን ላይ ያልተፈተኑ የግል ተማሪዎች ወደፊት በሚገለፅ ጊዜ በመስከረም 2016 ዓ/ም እንደሚፈቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።