Get Mystery Box with random crypto!

Ethio iselamic gerup

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioiselamdawa — Ethio iselamic gerup E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioiselamdawa — Ethio iselamic gerup
የሰርጥ አድራሻ: @ethioiselamdawa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 708
የሰርጥ መግለጫ

ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @dinuhamzabot
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-27 12:23:45 ጌታዬ ሆይ!!ጨንቆኛል አልኩህ (ከአላህ ራህመት ተስፋ አትቁረጡ አልክ!

....ካንተ ሌላ ማንም የለኝም አልኩህ (እኔ ከደም ስርህ የበለጠ ቅርብ ነኝ )አልክ

አትርሳኝ አልኩህ (አስታውሱኝ አስታው ሳቹሃለሁኝ)አልክ.....

.. ተስፋን ስጠኝም አልኩህ (ከችግርም ጋር ደስታ አለ) አልክ

...ህልሜ እንዴት እውን ይሆንልኝ ይሆን አልኩህ (ለምኑኝ እቀበላቹሃለው)አልክ

ጌታዬ ሆይ ጥራት ይገባህ ምን ያህል ቸር ነህ !!!

@Dinel_islam @Dinel_islam
153 viewsmahammedin hamza, 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 10:21:32 ምርጡን ጓደኝነት ላስተዋውቅህ ሀቢቢ....

ረሱል ሶለላ አለይሂ ወሰለም በኢስራ ወል ሚዕራጅ ጉዞ ሀድረተል ሙንተሀ ደርሰው ጅብሪል ከዚህ በላይ ማለፍ አልችልም ብሎ በተመለሰ ግዜ

.....አላህ ሱብሀነ ወተዓላ ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ብሎ ከዛ በላይ ያስጎበኛቸውን መላይካ ፊቱን በውዱ ጓደኛቸው በአቡበክር ሲዲቅ ፊት አስመሰለላቸው ያኔ ተረጋጉ!

@Dinel_islam @Dinel_islam
424 viewsmahammedin hamza, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 09:34:15 ሶሀቢዩ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?!

T.me/ahmedin99

የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) አንዴ ከጂሃድ እየተመለሱ በምሽት መንገድ ላይ ማረፍ ፈልገው አንድ ሸለቆዋማ አካባቢ ላይ ሰፈሩ። መላው ሰራዊት እንዲተኛና እንዲያርፍ ፈልገውም:—

" እኛ ልንተኛ ነው ማነው የሸለቆውን መግቢያ በመጠበቅ ከድንገተኛ የጠላቶቻችን ወረራ ሊጠብቀን ፈቃደኛ የሚሆነው ?"ሲሉ ጠየቁ።

በዚህን ጊዜ ሁለት ሶሀባዎች ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት ተስማምተው ስራ ጀመሩ ከዛም አንዱ ለሌላኛው "እኔ የሌሊቱን ግማሽ ልጠብቅ፣ አንተ ደግሞ ግማሹን ትጠብቃለህ ተራ በተራ እንተኛ"ተባባሉ።

በዚህም መሰረት አንደኛው ተኛ ሌላኛው እየጠበቀ ለይል ሰላት መስገድ ጀመረ። እየሰገደ ሳለ ቀን ላይ በተደረገው ጂሃድ ባለቤቱ የቆሰለችና ድንገት ከጉዞ ሲመለስ በዚህ ቆስላ ያገኛት ባሏ" ከነሱ መሀል አንድን ሰው ሳላቆስልና ደምም ሳላፈስ አልመለስም" ብሎ ዝቶ ከቤቱ የወጣው አይሁዲ ከነቢዩና ባልደረቦቻቸው ማረፊያ መግቢያ ላይ ሲደርስ እየሰገደና ጌታውን እያናገረ (ቁርኣን እየቀራ) የአላህን ባሮችን የሚጠብቀውን ሶሃቢይ ከቅርብ ርቀት ተመለከተው....በያዘው ቀስትም ወርውሮ ወጋው ሶሀቢዩም ቀስ አድርጎ አውጥቶት ሰላቱን
ቀጠለ፣ለሁለተኛ ጊዜም ደግሞ ወረወረ አሁንም ወጋው እንደመጀመሪያው ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሰላቱ ላይ ቀጠለ! በቀስት ሰውነቱን ቀጥታ እየተወጋ የማይወድቀውና የማይጮኸው ግለሰብ ሁኔታም እየገረመው ለሶስተኛ ጊዜ ወርውሮ ወጋው፣ ይህንም ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሩኩዕ ከዛም ሱጁድ አድርጎ ከአጠገቡ የተኛውን አብሮት የሚጠብቀውን ሶሀቢይ ቀሰቀሰው እንቅስቃሴያቸውን ሲመለከትም አይሁዲው ቦታውን ጥሎ ጠፋ....

ሌላኛው ሶሀቢይ ልክ ሲባንን ዙሪያው በደም ተሞልቶ ሲመለከት ምን እንደገጠመው ጠየቀው የሆነውን በነገረው ጊዜም "ታድያ ምነው ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደወጋህ አልቀሰቀስከኝም"? ሲልም ጠየቀው ይህ ልቡ በጌታው ቃል በቁርዓን ፍቅር የተሞላና ጥፍጥናውም ሁሉን ነገር ያስረሳው ውድ ሶሀቢይም "አንዲትን ሱራ ጀምሬ ነበር ሳልጨርሳት ማቆም አልፈለግኩም፣ ነቢዩ እርሳቸውንና ምዕምናንን የመጠበቁን ኃላፊነት ጥለውብኝ ባይሆን ኖሮ ነፍሴ እስካልወጣች ድረስ የሆነው ቢሆን ቁርዓኔን መቅራት አላቋርጥም ነበር" ብሎ መለሰለት!!!

ይህ ሶሀቢይ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?!
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)
943 viewsmahammedin hamza, 06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 09:25:58 የዓይን ምስክር ነኝ

ኡስታዝ በድር ሁሴን

በ1997 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የቅንጅት ፖርቲ ከፍተኛ አመራሮች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ልደቱ አያሌውና ሌላ ስማቸውን የማላስታውሳቸው የፖርቲው አመራር በሰሜን ሆቴል በጠሩት ስብሰባ ላይ ተገኝቻለሁ። በስብሰባው የተሳተፋት ሰዎች ቁጥራቸው ከአስር የማይበልጡ ተፅእኖ ፈጣሪ ተብለው የታሰቡ ሰዎች ናቸው።
የስብሰባው ዓላማ ስለ ቅንጅት ማንነት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ የተሰራጨውን "ፕሮፖጋንዳ" ማረምና ማስተካከል እንደሆነ ተነገረን። ስለ ፖርቲው ገለፃ ከተደረገልን በኋላ ሙስሊሙ ድምፁን ለቅንጅት እንዲሰጥ ጥሪ ተላለፈልን።

ከታሳታፊዎች ጥያቄዎች መቅረብ ጀመሩ። ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የመስጅድ ቦታ ጉዳይና የትምህርት ቤቶች ሂጃብ ክልከላ ይገኙባቸዋል። በርካታ መስጅዶች ህዝበ-ሙስሊሙ ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ያቆማቸው ናቸው። ሙስሊም ሴት ተማሪዎችም በሂጃብ ሳቢያ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ነው። እነኝህን ችግሮች ለመፍታት የምትከተሉት ፖሊሲ ምንድን ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ የፖርቲው አቋም ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ።

አቶ ልደቱ አያሌው መልስ ሲሰጡ ሙስሊሙ ለዘመናት የቆዩ ችግሮቹን ሌላ አካል እንዲፈታለት ከመጠየቅ ይልቅ ራሱ በፖለቲካው ውስጥ መሳተፍ እንዳለበት ጠቅሰው "ኑ join አድርጉንና አብረን ለለውጥ እንስራ" የሚል ምላሽ ሰጡን።
ዶ/ር ብርሃኑ በወቅቱ የሰጡት ምላሽ ከ17 ዓመታት በኋላ ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል፤ እንዲህ ነበር ያሉን:-

" እኔ የእስልምናም ሆነ የሙስሊም ጥላቻ የለኝም። አያቴ ሙስሊም ናቸው። ነገር ግን ሂጃብን በሚመለከት የለኝ አቋም የፈረንሳይ መንግሥት አቋም ነው። ይህንን በማለቴ የናንተን ድምፅ የማጣ ከሆነ ልጣው።"

ፈረንሳይ በሂጃብና በአጠቃላይ ኢስላማዊ መለያዎች ላይ የነበራትን/ያላትን አቋም ለሚያቅ ሰው ቁርጥ ያለ ምላሽ ነበር። ዶ/ሩ ሙስሊም ጠል አለመሆናቸውን ሊያስረዱ ጠርተውን ጠልነታቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አቋማቸውን አረዱን። የፖርቲው ወይም የሁሉም የፖርቲው አመራሮች እንደነበር ግልፅ ማስረጃ የለኝም። የዶ/ሩ አቋም ግን የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ግልፅ አድርጎልናል።

ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ስመለስ:-

ክቡር የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ያኔ ያንን አቋምዎን ስሰማ ያልኩትን ልንገርዎ፦ "እኒህ ሰው ጎበዝ ኢኮኖሚስት እንጅ ጥሩ ፖለቲከኛ መሆን አይችሉም" ነበር ያለኩት።

እርግጠኛ ነኝ እርስዎ ያስተምሩበት የነበረውና የፕሮፌሰርነት ማእረግ የሰጠዎ የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ለተማሪዎቹ መስገጃ ቦታ እንዳዘጋጀ፣ አለያም ለተማሪዎቹ የትምህርት ሂደቱን በማያሰናክል መልኩ እምነታቸውን practice እንዲያደርጉ ሙሉ ነፃነት እንደሰጠ ያውቃሉ።

ሸሪዓን መሰረት ያደረጉ የፋይናንስ ተቋማትን በሚመለከ ባለፈው ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ያንፀባረቁት አቋምና ስልጣን ቢይዙ እነኝህን ባንኮች የመገደብ ሃሳብ እንዳለዎ መግለፅዎ አሳዛኝ ሆኖ አልፏል። ምናልባት የብሄራዊ ባንክ ገዥ የመሆን እድል ቢያጋጥምዎ ይህንኑ አቋምዎን ሊጭኑ ነውን? በትምህርት ሚኒስትርንዎ እንዲህ ካንገላቱን ሃገር የማስተዳደር እድል ቢያገኙስ ምን ያደርጉን ይሆን?!
እናም እባክዎን በህዝብ ተመርጠው ሳይሆን ለፖለቲካ አካታችነት ሲባል የተሰጥዎን ስልጣን በ1997 የነገሩንን አቋምዎን ማራመጃ አያድርጉት። ከቻሉ የግል ፍላጎትዎንና ዝንባሌዎን ወደጎን ብለው ሰላትና ሂጃብ ሙስሊሞች የማይደራደሩባቸው የእምነታቸው ክፍል ስለሆኑ በአግባቡ የሚስተናገዱበት የህግ ማእቀፍ እንዲዘጋጅ ያድርጉ። ካልቻሉ ግን ሃገራችን ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ በላይ ሌላ መከራ መሸከም አትችልምና ስልጣንዎን በመልቀቅ ለሃገርዎ ውለታ ይዋሉላት።
550 viewsmahammedin hamza, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 10:57:14 #ረመዳን_11

አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ ላይ ነብያችን(ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-

"ብዙ ጿሚዎች አሉ፤ ከጾማቸው የሚያተርፉት መራብና መጠማትን ብቻ ነው።"

የጾማችን ምንዳ እንዳይቀንስ ለቀልድም ቢሆን አላስፈላጊ
ንግግሮችን (ባህሪያቶችን) ማሳየት አይኖርብንም።

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
1.0K viewsmahammedin hamza, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 13:56:43 እኔ ረመዳን ከመድረሱ በፊት ይቅርታ
ለመጠየቅ 1ኛ መሆን እፈልጋለሁ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""'""'"
•ምናልባት የሆነ ቀን ላይ ከራሴ ጋር ወይም ከሰዉ ጋር ሁኜ ሆን ብዬ ወይም ሳላስበዉ ብዙ ነገር አርጌ ይሆናል እናም፦

-ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያስቀየምኩአችሁ
-ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያማሁአችሁ
-ይቅርታ በኔ ምክኒያት ትንሽም ብቶን ያናደድኩአችሁ

በእርግጥ አላህ በሀሜት የተዘፈቀን ሰዉ የሚምረዉ የታማዉ አካል በይቅርታ ሲያልፈዉ እንደሆነ አዉቂያለሁ እና ይቅርታ (Awfu) ሳትሉኝ እንዳታለፉኝ
=እኔ ለአላህ ብዬ ይቅር (Awfu) ብይለዉ ።
*እንዲሁም መላኢካዎች በረመዳን ወር የተኮራረፉ ሰዎች ያሉበት ቤት ሲቀር ሁሉም ቤት ይገባሉ እስቲ ለማስታወስ ያክል እናንተስ ከማን ጋር ተቀያይማቹሀል (ተኮራርፈዋል) ?
ከአባት
ከእናት
ከወንደም
ከእህት
ከዘመድ
ከጎሮቤት
ከጓዋደኛ…… ከአሁኑ ለአላህ ብላቹህ ይቅር (Awfu) ተባባሉ
ይቅርታ ጥሪ ነዉና ነፍሳችንን ንፁህ እናድርገዉ ።
* አሁን ያለንበትም ሁኔታ አሳዛኝ ነዉ ድንገተኛ ሞት እጅግ በዝቷል አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን
@ በአካል የምታቁኝ በስምም ብቻ ይሁን የምታቁኝ ሁላችሁም ይሄን ፅሁፍ ያነበባችሁ በሙሉ ለፈጣሪ (ለአላህ) ብላችሁ ይቅር (Awfu) እንድትሉኝ እጠይቃችሁአለሁ
ይቅርታ
ይቅርታ
ይቅርታ
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh

921 viewsmahammedin hamza, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 09:36:41 #ሱረቱ አል-ፋቲሀ..........የአላህን ቁጣ ትከላከላለች::

#ሱረቱ ያሲን .........ከቂያማ ቀን ጥማት ትከላከላለች: :

#ሱረቱ አል-ዱኻን..........ከቂያማ ቀን ጭንቀት ትከላከላለች::

#ሱረቱ አል-ሙልክ..........ከቀብር ቅጣት ትከላከላለች::

#ሱረቱ አል-ካፊሩን..........በሞት ሰአት ከኩፍር ትከላከላለች::

#ሱረቱ አል ኢኽላስ..........ከኒፋቅነት
ትከላከላለች::

#ሱረቱ አል-ፈለቅ..........ከምቀኝነት
ትከላከላለች::

በቅንነት ቻናላችንን ሼር አድርጉልን
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)
817 viewsdi am sh ab Ma ba ek fe ze, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 14:49:35
918 viewsdi am sh ab Ma ba ek fe ze, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 13:55:43 አቡ ዓብደላህ ግመልህ
እንዴት ሆነች?

ከወጣት ሶሐቦች ውስጥ አንዱ ነው። ሳይሰልም በፊት ከአንዲት ኮረዳ ጋር ለየት ያለ ቅርርብ ነበረው። ኢስላምን ከተቀበለ በኋላ አንድ ቀን በመዲና ጎዳና ላይ ልጂቱ ጋር ተገጣጠሙ። አይኑን ሳይሰብር ፍጥጥ ብሎ፣ አንገቱን ጠምዝዞ እያየ መንገድ ስቶ ከግድግዳ ጋር ተጋጭቶ ደምም ፈሰሰው።

በዚሁ ሁኔታ ረሱላችን ጋር መጣሁ ይላል የዛሬው ኮከባችን ኸዋት ቢን ጁበይር (ረዐ)። ደሜን ሲያዩም "ምን ሆነህ ነው?" ብለው ጠየቁኝ። እኔም ስለሆነው ነገር ሁሉንም ነገርኳቸው ይላል። እርሳቸውም "እንዳይደግምህ። አላህ ለአንድ ባሪያው መልካምን ሲሻለት ቅጣቱን በዱንያ ያፈጥንለታል።" አሉት። (የጅህን ነው ያገኘኸው አሉት ) አይ ! ረሱል

ኸዋታችን አንድ ከበድ ያለ ገጠመኙን እንደሚከተለው ይነግረናል:- ነብያችን (ሰዐወ) ጋር መረ-ዞህራን (ለመካ ቅርብ ስፍራ ነው) የተሰኘ ስፍራ ላይ አረፍን። ካረፍኩበት ድንኳኔ ወጣ ስል ሴቶች ሰብሰብ ብለው ይጫወታሉ። በጣም ተመሰጥኩ። ተመልሼ ዘነጥ የሚያደርገኝን ልብስ ለብሼ ተቀላቀልኳቸው። (ከነርሱ ጋር እየተጫወትኩ፣ ስሳሳቅ) ነብያችን (ስዐወ) ከማረፊያቸው ድንገት ወጡ።

ሲመለከቱኝም "አባ ዓብደላህ ከነርሱ ጋር ምን ትሰራለህ ?" አሉኝ። በድንጋጤ ብርክ ያዘኝ። ምላሴ ተያያዘ። ድብልቅልቅ ያለ መልስ ሰጠኋቸው። ይላል። "አንድ እየደነበረ የሚሮጥ አስቸጋሪ ግመል አለኝ። ለርሱ ማሰሪያ ገመድ ፈልጌ ነው።" አልኳቸው።

እንድነሳ ካደረጉኝ በኋላ ለመፀዳዳት ሲሄዱ ተከተልኳቸው ይላል። ውዱእ አድርገው ከፂማቸው ውሃ እየወረደ መጡና። " አባ ዓብላላህ ግመልህ እንዴት ሆነ?" አሉኝ። ከዚያም ወደ መዲና ጉዟቸውን ቀጠሉ። ነብያችን ከዚያ በኋላ መንገድ ላይ ሲያገኙት ስለ ግመሉ በተደጋጋሚ ይጠይቁታል

መዲና ከደረሱ በኋላ ግን ኸዋት በጣም ስላፈረ ከመስጂድ ቀረ። እርሳቸው (ሰዐወ)፣ መስጂዱና ወንድሞቹ ሲናፍቁት አንድ ቀን ለናፍቆት ጭር ባለበት ሰዓት መስጂድ ገብቶ በተመስጦ ይሰግድ ጀመር። ነብያችንም(ሰዐወ) ከቤት ወደ መስጂድ ገቡና ቀለል ያሉ ረከዓዎችን ሰገዱ። ኸዋት መግባታቸውን ሲያውቅ እስኪወጡለት ድረስ ሰላቱን የባሰ አስረዘመው።

ሐቢባችን (ሰዐወ) ነቄ፣ ምርጥ ሙረቢና አስደናቂ ፍጡር አይደሉ " ኸዋት እንደፈለግክ አስረዝም፣ እኔ እንደሆንኩ ሳትጨርስ ከዚህ አልሄድም" አሉት።
አስቡት ሶላት ውስጥ ምን ሊያስብ እንደሚችል
ራሱ ይነግረናል " በቃ እውነቱን ተናግሬ ልገላገል ብዬ ወሰንኩ" ይላል። ቶሎ አሰላመተና ቀረባቸው። "አሰላሙ ዓለይኩም አባ ዓብደላህ ግመልህ እንዴት ሆነ?" አሉት። እርሱም " በእውነት በላኮት አምላክ እምላለሁ ከዚያ ቀን ጀምሮ ግመሉ አልፈረጠጠም" አላቸው። " አላህ ይዘንልህ" ብለውት ፋይል ዘጉ።

ነብያችን (ሰዐወ) ኸዋት እንዲህ ያለ ግመል እንደሌለው ያውቃሉ። ሴቶች ጋር የተቀመጠውም ቅፅበታዊ በሆነ ሰዋዊ ድክመት ምክንያት እንደሆነ ተረድተውታል። የለህም ዋሽተኸኛልም አላሉትም። ነገርግን በተደጋጋሚዋ ጥያቄያቸው ውስጥ "እውነቱን አውቄያለሁ ተናግራት" እያሉት ነበር። ጉዳዩንም በርሱና በርሳቸው መሃል ብቻ አስቀሩት። ህዝብ ፊት አላሰጡትም።

አማኝም ይሁን አስተባባይ፣ ታዛዥም ይሁን ስህተት ላይ የሚወድቅ ጥፋተኛ፣ አዋቂም ይሁን ጃሂል፣ ሃብታምም ይሁን ድሃ፣ መሪም ይሁን ተመሪ ብንሆን ዞረን ዞረን ሰዎች ነን። በውስጣችን የብዙ ስሜቶች ፍቅር አብሮን ተፈጥሯል። ገንዘብ፣ ተቃራኒ ፆታ ወዘተ። ክደን ሳይሆን በሰዋዊ ስህተት ገብተን እናምፃለን። ወንጀል ከነድንበሩ ወንጀል ነው። በልሳናችን፣ ተግባራችንና ህልውናችን ልንርቅና ልንጠየፈው ግድ ይላል።

እና ምን ለማለት ነው

ያንተ ሚና ሰዎችን ከፈጣሪያቸው ጋር በማስተዋወቅ፣ ጥቅምና ጉዳት በጉልህ ይታዩ ዘንድ የብርሃን ጨረር በመሰለጥ ላይ ብቻ የተገታ ነው። የሰዎችን ነውር ሸፍን እንጂ አታዋርድ። ከቻልክ እዘንላቸው ካልቻልክ ግን አላህ ወደርሱ ተጣሪው እንጂ ፍጡራኑን አላፈናፍን ባይ ተቆጣጣሪ አድርጎ ስላልሾመህ ቦታህንና አቅምህን እወቅ። ኃይማኖተኝነት (አማኝነት) ከሕይወት ራስን ማግለል ሳይሆን በውስጧ ሆኖ አላህ ወደሚፈልገው አቅጣጫ መንጎድ ነው።
አብዱሮህማን ስይድ (ሜጢ)
984 viewsdi am sh ab Ma ba ek fe ze, 10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 19:37:17 ‍ #አንድ_አፍታ

ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ

#share #share #share #share
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
#ልጄ_ሆይ ፧ በዝምታየ ተፀፅቼ አላውቅም ፡፡
•••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አታስገባ፡፡
•••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ምላስክን ‘አላህ ሆይ ‘ ማለትን አለማምድ ለአላህ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታት• አሉትና፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ፧ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች ፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ከመገረም ጋር አትሳቅ; ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ሁለት ነገሮችን አታውሳ ፧ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና ፣ ለሰዎች ያደረከውን መልካም ነገር፡፡
••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ በጣም ጣፋጭ አትሁን ከንቀት እንዳትበላ መራራ አትሁን እንዳትተፋ ፡፡
•••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ ; ከምትመገበው ለውሻ ብጥለው የተሻለ ነው ፡፡
••••••••••••••••
#ልጄ_ሆይ ፧ የአላህን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው ; ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡፡
join as

ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)
877 viewsdi am sh ab Ma ba ek fe ze, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ