Get Mystery Box with random crypto!

ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነታችን እንደ ወንዝ ይሁ | ስብዕናችን #Humanity

ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነታችን እንደ ወንዝ ይሁን! ሳንመርጥ፣ ለለመነን ሁሉ እጃችንን እንዘርጋ። ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ይመሰክራል፤ የኛም ደግነት እንዲሁ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ፤ ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት የተሞላበት ይሁን።

መርዳት ዕድል ነውና እንጠቀምበት! ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የለም  ለፈጣሪ እጅ ሆነን እንደምንሰጥ ልናስብ ይገባናል። እውነተኛ ስጦታ ከትርፍ ሳይሆን ካለን ላይ ነውና ተጎድተን እስክንሰጥ ድረስ ገና እንዳልሰጠን ልንረዳ ይገባል፡፡

እያዩ ፈንገስ በመድረኩ ላይ ሲናገር

"ላለመርዳት ኪስህን ሰበብ አታድርግ። ባዶ ኪስ ነህ ማለት የምትሰጠው ምንም ነገር የለህም ማለት አይደለም፤ ቢያንስ የምትሰጠው ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ አለክ ማለት እንጂ።

ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ መስጠት ቢያቅትህ፥ በባዶ ኪስህ እጁን እንዲያስገባ ፍቀድለት። ቢያንስ አንድ እጁን ከብርድ ትከላከላለህ'' ይለናል ።

እናም ወዳጄ ሰው ሁን

ሰውን እንደራስ ለመውደድ ቅን አዕምሮ፤ ደግ ልብ ይፈልጋል፡፡  አንተም ፈጣሪን የምትሻ ከሆነ ወደ እሱ ቤት መሄድ አለብህ። ቤቱም የሰው ልጅ ሁሉ ነው ፤ አስተውል ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ፡ የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና የተራቡትንም ሽራፊ ቁራሽ አትንፈግ የታመመን ጠይቅ፣ የተቸገረን እርዳ፣ አግዝ ታማኝ ሁን! በዚህ ልክ ለፈጣሪ ስትቀርብ፣ ስኬትህም ሆነ በረከትህ ወዳንተ ይመጣሉ።

ፈጣሪ ለሁላችንም ልበ ሰፊና ቅን ልቦና ይስጠን!

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot