Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዱ ሰው ዛሬ የሚኖርበት ቀን ትናንቱ ነው:: ትናንት ወድቆ ነበር፣ ተሳስቶ ነበር ፡፡ ትናንት | ስብዕናችን #Humanity

አንዳንዱ ሰው ዛሬ የሚኖርበት ቀን ትናንቱ ነው:: ትናንት ወድቆ ነበር፣ ተሳስቶ ነበር ፡፡ ትናንት የሆነ ነገር በህይወቱ አልፏል፡፡ ትናንቶቹ በትዝታ እየመጡ ዛሬውን ይነጥቁታል፡፡ የሰው ልጅ ውድቀቱ ብቻ ሳይሆን ስኬቱም ጠላቱ ነው ይባላል፡፡

በረጋ ውሀ ላይ ሁሉም ሰው ጎበዝ ካፒቴን መሆን ይችላል፤ግን የእውነተኛው ካፒቴን ችሎታ በማእበሉ ጊዜ ይታያል፣ እንደሚባለው ሁሉ የህይወታችንም መሪነት ትናንት አሁንና ወደፊት በገጠሙንና በሚገጥሙን መሰናክሎች ይፈተናል። የውስጥ ጥንካሬያችንም በነዚሁ ጊዜያት ይፈተሻል።

የተሳካ ህይወት መኖር የማይፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሁሉም ሰው ታሪክ መፃፍ ይፈልጋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ራሱን መመርመር አለበት ፣ የሰው ልጅ ከፍታና ዝቅታ፣ መነሳትና መውደቅ በሚገነባው የስብዕና ጥንካሬ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን በምናወራበት ሰዓት ነገ ብለን ስናስብ፣ ጊዜያችንን አዲስ ማድረግ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም አእምሮዋችን ስላለ ፣ አእምሮዋችን ሁሉን ያስታውሳል፡፡

እራስን መለወጥ ቀላል ጉዞ አይደለም። እንደ አብዮት ቆጥረን ለዘመናት ተብትቦን የኖረውን ማንነት ገርስሰን መጣል አለብን ፣ ደካማው ማንነታችን ወርዶ ስኬታማው ማንነታችን ሊነግስ ይገባዋል።

ብዙዎቻችን ውስጣችን ትርምስምስ ብሏል፤ የምንፈልገውን አናውቅም፤ የምንራመድበትን መንገድ አናውቅም፤ ብዙ ሃሳቦች በውስጣችን አሉ፤ ግን በየትኛው ሃሳብ ጸንተን እንኑር? ለዚህ ነው በራሳችን ላይ አብዮት መጥራት
የሚያስፈልገን። ህይወት እጅግ አጭር ናት፤የፈለግነውን አይነት ኑሮ ለመኖር፤ እራሳችንን መለወጥ ግድ ይለናል፤ ደካማውን ጥለን፤ መልካሙን እኛነታችንን ልንተክል ጊዜው አሁን ነው።

           ውብ ቅዳሜ

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot