Get Mystery Box with random crypto!

ያለፈበት ብቻ ያውቀዋል!! ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱን ሰዎች ስለ ትናንት ህይወታቸው ስትጠይቃቸው | ስብዕናችን #Humanity

ያለፈበት ብቻ ያውቀዋል!!

ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱን ሰዎች ስለ ትናንት ህይወታቸው ስትጠይቃቸው ሁሉም ፊት ላይ ደስተኝነትን አታነብም:: ሁሉም በእምባ እናም በትጋዜ ተሞልተው ይነግሩሀል፣ ከሙቀት ዋሻህ ውስጥ የምትወጣበት፣ከተወዳጅነት አጀብታ ለነፍስህ ፍላጎትና ለህልምህ የምትወርድበት ጥልቁና አስፈሪው የህይወት መንገድህ ነው።

ያስፈራል ልብ ያርዳል ነገር ግን ነፍስን ለጥበብ ይቀርፃል። በዛ ውስጥ ሰው ይርብሀል ።ተቃዋሚህ ይበዛል:: እጅ ጠቋሚው ተሳላቂው ይከብሀል:: ብታወራ የሚረዳህ አንዳች አይኖርም!! የሚፈርድ እልፍ ይሆናል...ህመሙ ጥልቅ! የስሜት ጉዳቶቹም ብርቱዎች ናቸው።

ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ትልቅ ህልም እያላቸው ትንሽ ሆነው መኖርን የሚመርጡት!አስፈሪውም ትልቅ ህልምህ ወደ ትልቅነት የሚመራህ በትናንሽ የህይወት ጉዳዶች ውስጥ መሆኑም ነው። ብቻህን የምታለቅስበት ብቻህን የምትፋለምበት ብቻህን ሞትን ምትናፍቅበት ግን ደግሞ ብቻህን የምትዘምርበት ብቻህን የምትፀልይበት ብቻህን አምላኬ ብለህ ከፈጣሪህ ጋር የምትነጋገርበትም መንገድ ነው።

መከራ የፈጣሪ ትህምርት ቤት ነው። "ስቃዮች መገፋቶች መድከሞች መውደቆች  ሁሉም የነፍስ ጥልቅ ህመሞችህ በስተጀርባ መምህሩ አምላክህ አለ።ለዛም ነው ማስተርስ ጫንኩኝ ከሚለው ሰው በተሻለ ህይወት ያስተማረቻቸው አለምን ሲመሩ ሲቆጣጠሩት የትምመለከተው!

''ሰውን ካስተማረው ፈጣሪ በጥበብ አስውቦ የቀረፀው ይበልጣል'' ከሙቀት ጎጆህ ስትወጣ! ህልምህን ከፈጣሪህ ምሪት ጋር ትከተለዋለህ! የግድ ይሆንብሀል አማራጭ ታጣለትህ ብትቀመጥ የሚወጋህ ሺ ስለሚሆን ይግድ ትጓዛለህ እየዛልክ ትጠነክራለህ እየሞትክ ህያው ትሆናለህ እየወረድክ ከፍፍ ትላለህ የግድ ይሆንብሀል...!

ህይወት ፊቷን የምምትሰጠው ጠንካራ ጡንቻ ላላቸው ሳይሆን ጠንካራ መንፈስ ላላቸው ነው። ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን
ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት
ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን።

ወደ ቁልቁለቱም ድፈር! ወደ አስፈሪው መንገድ በድፍረት ጥለቅ ፣ አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር....። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል።

የህይወትህን ሲኦል ካልተጋፈጥክ የስኬትህን ብርሀን መቼም አትለብሰውም ፣ የከፍታውን መንገድ በመውርደት ፣ የደስታውን መንገድ በሀዘን ፣ የንግስናን መንገድ በባርነት ፣ የመሪነትን መንገድ በተመሪነት ፣ የስኬትንም መንገድ በውድቀት በኩል ውስጥ ትገናኛቸዋለህ!

አለም ለደፋሮች ታደላለች። ወደ ከፍ ያለ ማንነት ጉዞ ፣ስትጀምር የነፍስክ ጥንካሬ ተአምራዊ ወደ ሆነ ቦታ ያደርሥሀል፣ ድፋር ሁን! ለህልምህ ቆራጥ ሁን ፣ የህይወት ብርሀንህ የሚወለደው ከዛ እርምጃህ ነው!

ዉብ ጊዜን ተመኘን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot