Get Mystery Box with random crypto!

ቃል አልባው ቃል ኪዳን! እውነተኛ ጓደኝነት ያስደምመኛል! እንደዛሬው ማህበራዊ ድረ ገፁ 'ጓደኛ | ስብዕናችን #Humanity

ቃል አልባው ቃል ኪዳን!

እውነተኛ ጓደኝነት ያስደምመኛል! እንደዛሬው ማህበራዊ ድረ ገፁ "ጓደኛ" የሚለውን ቃል ሳያልከሰክሰው በፊት ...ጓደኝነት ቀለል ተደርጎ የሚወሰድ ግን ደግሞ እጅግ ጥልቅ የሆነ የመንፈስ ትስስር ያለውን ግንኙነት መግለጫ ቃል ነበር! ጓደኝነት መሠረቱ ውበት አይደለም ፣ ጥቅም አይደለም፣ ወሲብ አይደለም፣ ማህላና ቃል ኪዳን አይደለም፣ ተስፋም አይደለም! ከፍቅረኝነት  በላይ የሚያስደምም ነገር አለው!

ጓደኞች በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ንፁህ የነፍስ መዋደድ ብቻ ነው! አንዱ ለሌላኛው መቆም ነው! ላልከዳህ ላልከዳሽ የሚል ማህላ የለበትም! ከመሀላ የጠነከረ ያለመካካድ እና የእድሜ ልክ አብሮነት ግን በውስጡ አለ! ጓደኝነት ፆታ ፣ ባህል፣ እምነት፣ ርቀት የኑሮ ደረጃ አይወስነውም! አንዱ ለሌላው ህይወትን እስከመክፈል የሚደርስ ፍቅር በጓደኝነት ስሜት ውስጥ አለ!

ጓደኝነት ብዙ ያልተዘፈነለት፣ ብዙ ያልተገጠመለት ብዙ ያልተፃፈለት ብዙ ፊልም ያልተሰራለት ግን ደግሞ በህግ ያልታጠረ እውነተኛ ፍቅር የተሞላበት ስሜት ነው! ጓደኝነታችሁን አታፍርሱ! ቃል አልባ ቃልኪዳን ነውና ለጓደኞቻችሁ ሚስጥርና ሁለንተናዊ ደህንነት ታምናችሁ አብሮነታችሁን አጠንክሩ!

አሌክስ አብርሃም

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot