Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ያስገርማል , የኑሮ ትንሽ የለውም, እዛ የወደቀችው ሳር አስገራሚ ናት | ስብዕናችን #Humanity

ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ያስገርማል , የኑሮ ትንሽ የለውም, እዛ የወደቀችው ሳር አስገራሚ ናት ወፍ ለቅሞ ጎጆ ይሰራባታል ። ይሄን ሳር አጭዶ ያመጣው ማጭዱ አስገራሚ ነው ሰዎቹ ማጭድ ማሰባቸው ?! የሚያስገርመው ጉዳይ እልፍ ነው . .
ሳሩን አጭዶ ያመጣልኝ ሰውዬ ዘገየ ይባላል , ጨዋታ ያውቃል እሱ ሲያወራኝ የሚገርም ነው ታሪኩ : 'ለምን ?' ብትል እንዲያው ወንድ ሆነ እንጂ ታሪኩ ተኔ አንድ ነው።

የእኔ ታሪክ ምንም ብለፋ፣ ምንም ብቀባጥር የእኔ ብቻ አይሆን 'ለካ የእሱ የእኔን ይመስላል!' ብለህ መታዘብ አለ ... ያንተ የአንተ ከሆነ ፣ የእናትህ የእናትህ ከሆነ፣ የሰብለ የሰብለ ከሆነ፣ እንዴት እዚህ ደረስን ? እሱ እኮ ነው!

"ጠዋት እዚህ ፀሐይ ስሞቅ የቆረጥኩት የአውራ ጣቴ ጥፍር ለስንት ጉንዳን እራት ይሆናል . . ? ባላርስም አበላሁ ማለት ነው ?!

ትሰማኛለህ ? . ሰሚ ካገኘ የማንም ታሪክ ይገርማል !

አዳም ረታ መረቅ

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot