Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ ሆይ ሰውው ሁንን…. አስተውል! ቆሞ መሄድህ መብላት መጠጣትህ ጥሩ መልበስ ጥሩ መናገር ወይን | ስብዕናችን #Humanity

ወዳጄ ሆይ ሰውው ሁንን…. አስተውል!
ቆሞ መሄድህ መብላት መጠጣትህ ጥሩ መልበስ ጥሩ መናገር ወይንም ሀብት ክብርና ዝናህ ያንተን ሰውነት በፍጹም ሊያረጋግጡልህ አይችሉምና፡፡ ይልቅ አትዘግይ! አሁኑኑ ራስህን ፈልግ.. ዙሪያህንም አስስ..

ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ፡ ጊዜህን ባግባቡ ተጠቀም ከሚያጸጽቱህ ነገሮች ቀድመህ ለመቆጠብ ሞክር ለህሊናህ እንጅ ለስሜትህም አትገዛ ላለፈ ነገር እየተጸጸትክ ቀሪ ጊዜህን አታባክን፤

ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡ የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና የተራቡትንም ሽራፊ ቁራሽ አትንፈግ፡ ባይኖርህም ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና!!
ለወሬ እጅ አትስጥ በጉዞህ ሂደት ውስጥ ለሚጮሁ ዉሾች ሁሉ አትደንግጥ አላማህን ለማሳካት በጽናት ጉዞህን ቀጥል  

ችግር መከራ ስቃይና ደስታንም አምኖ ለመቀበል ራስህን ዝግጁ አድርግ፤ ክፉን በክፉ ለመጋፈጥ ከመሞከር ይልቅ ውስጥህን በይቅርታና በመጸጸት ከተንኮል አጽዳ ፡፡  ከሰወች ጉዳትና ሞት ደስታን ወይም ሃብትን አትሻ!አትጠራጠር ያኔ! የንጹህ ልብ ህሊናና የዘላለም ደስታ ባለቤት የሃብታሞች ሁሉ ሃብታም …. የሰውም ሰው ነህ !!

በአብርሃም አባቡ

ውብ  አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot