Get Mystery Box with random crypto!

ቢላ ካልተሞረደ ዶልዱሞ እንደሚቀር ሁሉ የሰውም ልጅ ጠንካራና ብልህ እንዲሆን በተለያዩ ውጣውረድ ማ | ስብዕናችን #Humanity

ቢላ ካልተሞረደ ዶልዱሞ እንደሚቀር ሁሉ የሰውም ልጅ ጠንካራና ብልህ እንዲሆን በተለያዩ ውጣውረድ ማለፍ ግድ ይለዋል።እኚ ውጣውረዶች በሕይወታችን ውስጥ መከሰታቸው ተፈጥሯዊ ነው፣ እኛኑ ለማጎበዝ እኛኑ ለማንቃት እኛኑ ለማጠንከር እኛኑ ለማጀገን ነው ፣የዶሎዶመ ቢላ ለመቁረጥ ከማስቸገርም አልፎ ድካም ነው የሚሆንብን እንጂ እንደተመኘነው አይቆርጥልንም።

ያልተፈተነ ማንነትም ከተራራው ጫፍ የሚያደርስ ጽናትን አያላብሰንም። እውነታው መሞረድ ነው እውነታው መሳል ነው፣እውነታው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፍና ራስን ማጠንከር ነው። የሰው ልጅም ዛሬ በሁኔታዎች እራሱን እየፈተነ ማንነቱን ያጠነክራል። ዛሬ በሁኔታዎች ልቡን እያጠነከረ ለነገው ይዘጋጃል፣ዛሬ በሁኔታዎች መንፈሱን እያጠነከረ የወደፊቱን መንገድ በቀላሉ ያቅዳል።

ውስጣችንን አጠንክረን የገባንበትን ፈተና በድል እንወጣው። ቁስላችን ስብራታችን ውድቀታችን ሁሉ ያጠነክሩናል እንጂ አይገሉንም፡፡

ውብ  አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot