Get Mystery Box with random crypto!

``ክፉ ቀን ጥሩ ነው´´ ፕሮፌሰር መስፍን 'አገቱኒ ተምረን ወጣን' በሚለው መጽሀፋቸው ስለ ክፉ | ስብዕናችን #Humanity

``ክፉ ቀን ጥሩ ነው´´

ፕሮፌሰር መስፍን "አገቱኒ ተምረን ወጣን" በሚለው መጽሀፋቸው ስለ ክፉ ቀን እንዲህ ይላሉ፡፡.....

ክፉ ቀን ጥሩ ነው መማር የፈለገውንም ያስተምራል ፈጣሪ ሀያላን ነን የሚሉትንም ያስተምራል፡፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ደጋግ ሰወችን ይቀሰቅስና የግፍን መራራነት እንዲቀንሱት ያደርጋል፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው በተለያየ የኑሮ ደረጃ የተከፋፈሉትን በአላማ ያያይዛቸዋል፡፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው የግፍን ጥርስ ሁሉም እንዲያየውና እንዲንቀው ያደርጋል፡፡

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ብዙ ጉድ ያሳያል።የተማረውና የተመራመረው አምሮውን በኦሞ ሙልጭ አድርጎ አጥቦ ህሊናውን በጨጓራው አፍኖ የሆነውን አልሆነም እያለ ለልጆቹ ሀፍረን ሲሆን ያሳየናል።
-
ክፉ ቀን ጥሩ ነው ያለፈውን ካለው ጋር በእውነት እንድናወዳድረው ያስገድደናል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክብርን ወደ ውርደት ውርደትን ወደ ክብር ይለውጣል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው የጉልበተኛውን ልብ ያደነድናል አእምሮውንም ደርግሞ ይዘጋዋል የጭካኔውንም ወሰን የለሽነት ያሰየናል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ጥሩ ቀንን እየጮኸ ይጣራል።

ክፉ ቀን ጥሩ ነው የወደቀውን ለድል የጣለውን ለውድቀት ያዘጋጃል

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክፋት በጎነትን አሸንፎ እንደማይዘልቅ ያሳያል ህግ ቀልቡ ሲገፈፍ ዳኝነት ሚዛን ሲያጣም ያሳያል

ክፉ ቀን የጠራ መስትዋት ነው መልካችንን ብቻ ሳይሆን ባህሪያችንንም ጤናችንን ብቻ ሳይሆን ህመማችንንም ውበታችንን ብቻ ሳይሆን አስከፊነታችንንም ቁልጭ አርጎ ያሳየናል

ክፉ ቀን ጥሩ ነው ባጠቃላይ የመጪው ጥሩ ቀን ምልክት ነው።

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot