Get Mystery Box with random crypto!

ካህሊል ጂብራን የምንኖርበትን አለም በደንብ የሚገልጽ ድንቅ አባባል አለው። ' ደስታ እና ሀዘን አ | ስብዕናችን #Humanity

ካህሊል ጂብራን የምንኖርበትን አለም በደንብ የሚገልጽ ድንቅ አባባል አለው። " ደስታ እና ሀዘን አይነጣጠሉም፤ በአንድ አንገት ላይ የበቀሉ ሁለት እራሶች ናቸው" ብሏል።

ምንም አወንታዊ ብንሆን፤ ምንም የእምነት ሰው ብንሆን ምንም የተማርን እና የተመራመርን ብንሆንም፤ ከህይወት መፈራረቅ አናመልጥም። ከሀዘን እና ከደስታ፤ ከስኬትና ከውድቀት ቅብብሎሽ አንድንም። ይህ እውን ከሆነ የምንለውጠው በዙሪያችን ያለውን ሳይሆን፤ በውስጣችን ያለውን ነው።

ችግር አታሳየኝ ከማለት ችግርን የማልፍበት ጽናቱን ስጠኝ ብንል፣ አልውደቅ ሳይሆን ስወድቅ የምነሳበት ጉልበት ይኑረኝ ብንል፣በሩ አይዘጋብኝ ሳይሆን እሲከከፈትልኝ ድረስ የማንኳኳበትን ትዕግስት ስጠኝ ብንል፣ፈተና አይግጠመኝ ሳይሆን ፈተናውን የማልፍበትን ጥበብ ይግለጽልኝ
ማለት ብንጀምር የውጭውን አለም መቆጣጠር ቢያቅጠን ወሳኝ የሆነው የራሳችን አለም ላይ ሰላም እናሰፍናለን። ሰው በአስተሳሰቡ ይኖራል፤ የህይወት እይታውም ሆነ እጣፋታው የሚወሰነው በአስተሳሰቡ ነው። መልካም ኑሮ በመልካም አስተሳሰብ ይገነባል።

የትኛውም የህይወት ጎዳና ላይ ብንቆምም፤ ወደፈልግንበት መዳረሻ የመሄጃው እድል ዛሬም አለን። ቀዳሚው ተግባር ግን አስተሳሰባችን ላይ መስራት ነው።

ሚስጥረ አደራው

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot