Get Mystery Box with random crypto!

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ሞተዋል የሚለውን ዜና አስተባብለዋል፡፡ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ | Ethio Fm 107.8

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ሞተዋል የሚለውን ዜና አስተባብለዋል፡፡

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እሁድ ምሽት በትዊተር ገፃቸው ከኮቪድ 19 ጋር በተገናኘ ለቀናት ራሳቸውን ማግለላቸውን አሳውቀዋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ መግለጫቸው በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ ህይወታቸው አለፈ መባሉን አስተባብለዋል፡፡

ሙሴቬኒ በፈረንጆቹ ሰኔ 7 በቫይረሱ መያዛቸውን እና ራሳቸውን ማግለላቸውን አሳውቀዋል፡፡

"ሰላም፣ አሁን የኮሮና ሁኔታዬ አምስት ቀን ሆኖታል፣ ትላንት ምሽት እስከ ሌሊቱ 10 ሰአት ድረስ በደንብ ተኝቻለሁ" ሲሉ የዩጋንዳው መሪ በረዥሙ የትዊተር ጹሁፋቸው አስፍረዋል፡፡

ኡጋንዳውያን ለኮቪድ ክትባት እና ለተጨማሪ ክትባቶች በተለይም ለአረጋውያን ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

ሙሴቬኒ ወደ ከፍተኛ ህክምና መወሰዳቸው እና መሞታቸውን በትዊተር ላይ ባለፉት ጥቂት ቀናት ሲዘዋወር ሰንብቷል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ወር ኮቪድ-19 በይፋ ከአሁን በኋላ የአለም የጤና ድንገተኛ አደጋ እንዳልሆነ ገልጾ፣ ቫይረሱ ግን ባህሪውን መለዋወጡን ቀጥሏል ማለቱን ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos