Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞዉ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርሉስኮኒ በ 86 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተ | Ethio Fm 107.8

የቀድሞዉ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርሉስኮኒ በ 86 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የቀድሞ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲርቪዮ ቤርሌስኮኒ በደም ካንሰር ምክንያት በ86 አመታቸው በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡

ከሳምታት በፊት ሆስፒታል ገብተው የነበሩት ስሊቪዮ ቤርሌስኮኒ እየታከሙበት በነበረው ሳን ራፋኤል ሆስፒታል መሞታቸው ተዘግቧል፡፡
ቤርሌስኮኒ የጣሊያን ሴርኤ ላይ የሚገኝው የኤሲሚላን ባለቤት የነበሩ ሲሆን ከአመታት በፊት ክለቡን ለሌላ ባለሃብት መሸጣቸው ይታወሳል፡፡

በርካታ ካምፓኒዎች እና ድርጅቶች በስማቸው እንዳላቸው ይታወቃል፡፡
በአወዛጋቢነታቸው የሚታወቁት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤርሌስኮኒ ለሶስት ተከታታይ አመታት ጣሊያንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡

ቢሊዮነሩ በርሉስኮኒ ጣሊያንን ከፈረንጆቹ 1994 እስከ 2011 በጠቅላይ ሚንስትርነት አገልግለዋል፡፡

(በእስከዳር ግርማ)

አርቲ ኒዉስ

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos