Get Mystery Box with random crypto!

በ2016 በጀት ዓመት ሁሉንም ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንዲገቡ ይደረጋ | Ethio Fm 107.8

በ2016 በጀት ዓመት ሁሉንም ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ፡፡

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከመደበኛ አገልግሎታቸው ተስተጓጉለው ከነበሩ ዩኒቨርስቲዎች ውጪ ያሉት ዩኒቨርስቲዎች ፣ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንዲገቡ እንደሚደረግ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

እስካሁን 44 ከሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉት ሁለቱ ብቻ መሆናቸውንም የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበበ አለሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

እነዚህም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ መሆናቸውን ያስታወቁት ሃላፊው፣ በቀጣይ ቀሪ ዩኒቨርስቲዎችን በስርዓቱ እንዲካተቱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በሌሎች አገልግሎቶች የተሰማሩ ተቋማት 74 የመንግስት ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት ውስጥ እንደተካተቱም አቶ አበበ ገልፀዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos