Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ነጥብ አምሰት ቢልየን ብር የፈጀው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ በ | Ethio Fm 107.8

አንድ ነጥብ አምሰት ቢልየን ብር የፈጀው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ወደ ሥራ ገብቷል።


የሆቴሉ ግንባታ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢልየን ብር በላይ እንደፈጀ ባለቤቶቹ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።


ሆቴሉ አሁን ላይ በአጠቃላይ ከ 250 ዜጎች በላይ የስራ ዕድል እንደፈጠረም ታውቋል።

የኤሌትሪክ መኪና ይዘው ለሚመጡ ደንበኞቹ ኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ቦታ እንዳለውም በመግለጫው ተነስቷል።

በተጨማሪም ሆቴሉ የሚጠቀመውን የከርሰ ምድር ውሃ ለአካባቢው ነዋሪዎች ውሃ በነፃ እያደለ መሆኑም ተጠቅሷል።

በቅርቡም ለአካባቢው ነዋሪዎች ዳቦ በተመጣኝ ዋጋ ያቀርባል ተብሏል።

በአባቱ መረቀ

ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።