Get Mystery Box with random crypto!

ሙዚቀኛው ዳዊት ፍሬው ሀይሉ በአረፈበት ሆቴል ሞቶ ተገኘ ... በመሳሪያ የተቀነባበሩ አልበችሞን | Ethio Fm 107.8

ሙዚቀኛው ዳዊት ፍሬው ሀይሉ በአረፈበት ሆቴል ሞቶ ተገኘ
...
በመሳሪያ የተቀነባበሩ አልበችሞን በማሳተም እንዲሁም በርካታ መድረኮች ላይ የሙዚቃ መሳሪያ በመጫዎት ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈው የአንጋፋው ድምፃዊ ጋሽ ፍሬው ሀይሉ ልጅ ሙዚቀኛው ዳዊት ፍሬው ለስራ በሄደበት ጣሊያን ሮም ትላንት ምሽት በአረፈበት ሆቴል ተነግሯል ።

ሙዚቀኛው በኢትዮጵያ ኤምባሲ በጣሊያን ሮም ከተማ ስራዎቹን አቅርቦ ወደ አረፈበት ሆቴል ከገባ በኋላ ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ ማረፉን የጣሊያን ፖሊሶች ተናግረዋል።

በጣሊያን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የሞያ አጋሮቹ ከሀገሪቱ ፖሊስ ጋር ተነጋግረው የአርቲስቱን አስክሬን በሀገሩ ለማሳረፍ እንቅስቃሴ መጀመራቸውም ታውቋል::

ዳዊት ፍሬው የክላርኔት የሙዚቃ መሳሪያውን እየተጫወተ የሰራው ሶስት የሙዚቃ አልበም ያለው ሲሆን የአንጋፋው ድምፃዊ ፍሬው ሀይሉ ልጅም ነው።