Get Mystery Box with random crypto!

አባይ በረሃ ላይ የደረሰ አሳዛኝ የመኪና አደጋ አባት እና ልጅ አብረው ይሰራሉ አባት ሾፌር ልጅ | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

አባይ በረሃ ላይ የደረሰ አሳዛኝ የመኪና አደጋ

አባት እና ልጅ አብረው ይሰራሉ አባት ሾፌር ልጅ ረዳት ሆነው ኑሮን ለማሸነፍ ቤተሰብን ለመደገፍ ይደክማሉ የካቲት 26/06/2015 ግን ለአባት እና ልጅ መልካም አልነበረም ጭነት ጭነው አባይ በረሃን እየወረዱ ባለበት ሂደት መኪና ፍሬን እምቢ ይላቸዋል አባትም በእሳቸው በኩል ገደል በልጃቸው በኩል ተራራ መሆኑን ያያሉ በልጃቸው በኩል ቢያጋጩ የልጃቸው ህይወት መጥፋቱን ግምት ውስጥ በማስገባት ልጃቸውን ዘለህ ውረድ በማለት በእሳቸው በኩል መኪናውን ይጥላሉ መኪናውም ገደል ይገባል የሾፌሩም ህይወት ያልፋል።

አባት ልጃቸውን ታድገው በራሳቸው በኩል ጥለው ወደ ጥልቁ ገደል ገብተው ላይመለሱ ለዘልአለም አሸልበዋል አባት ለልጁ ምን እንደሆነ በተግባር አሳይተዋል።

(ሰጡ ብርሃን)