Get Mystery Box with random crypto!

የመውጫ ፈተና #ExitExam   የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

የመውጫ ፈተና

#ExitExam   የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያገኙትን መረጃ እናጋራቹህ

1. #ጥያቄ፡- የመዉጫ ፈተናው የሚሰጠዉ ከምርቃት ቧላነዉ ወይስ በፊት?

#መልስ፡- የመውጫ ፈተና አንድ ተመራቂ ተማሪ ከመመረቁ በፊት በትምህርት ህግ ማሟላት ያለበት መስፈርት ሰለሆነ ፈተናዉ የሚሰጠዉ ከ ምርቃት አስቀድሞነዉ፡፡

2.#ጥያቄ፡- ፈተናው በኦንላይንነዉ ወይስ ወረቀት?

- #መልስ፡- ፈተናው የሚሰጠዉ  ኦንላይንነዉ። ሁሉም ጥያቄዎች ምርጫ ብቻ ናቸው።የሒሳብ ጥያቄዎችም ስለሚኖሩ ተማሪዎች ወረቀት እና ኢስክሪፕቶ ይዞ ይገባሉ።

3.#ጥያቄ: - ፈተናዉ የሚሰጥብት በቋሚነት መቼነዉ?

#መልስ፡- ከ ሰኔ 20 እስከ ሐምሌ 20 ባሌ ጊዜ ዉስጥ ይሰጣል

4.#ጥያቄ፡ ስለ ሞጁል የተነሳ ጥያቄ

- #መልስ፡-የተለያዬ ሞጁል ሆኔ የሚለዉ ተማሪዉ ጊዜዉን ሰያባክን በዲፐርትመንት በኩል በሰነድ መልክ የተላከለትን (Core Competencies) ላይ ተመርኩዞ ተጨማሪ የማንበቢያ ማቴሪያሎችን እና የሚሰጡ ቲቶሪያሎችን በመከተታል ለፈተናዉ መዘጋጀት ይችላል ፡፡

5 #ጥያቄ፡- በፈተና ወቅት የሚሰጠዉ ሰዓት አጠቃቀሙ ምን ይመስላል የሚላዉ ነዉ፡፡

#መልስ፡- ለዚህ ፈተና አዲስ ሶፍትዌር ተፈብርኮ ተዘጋጅቷል። ለዚሁ አላማ ተብሎ የተዘጋጀ ማለት ነዉ።አዲስ ሶፍትዌር ለየት ሚያደርገዉ ለአንድ ጥያቄ ብቻ ሰዓት ሰጥቶ የሚያልፍ ሳይሆን ለአጠቃላይ ጥያቄ የተሰጠዉን ሰዓት ተፈታኙ ሚችለዉን ጥያቄዎችን እንዲሰራ ሙሉ ሰዓቱ የተሰጠዉ እስኪያልቅ የሚጠብቅ እና አስተራረሙ ደግሞ ተማሪው ሙሉ መዉጫ ፈተናውን ከጨረሰ በኋላ ነው ዉጤቱን የሚያየዉ፡፡እዛዉ ይታረማል ከፈተና ክፍል ሳይወጣ የሚለዉ ወሬ ሀሰት ነዉ ሁሉንም የትምህርት ፈተናዎችን ከጨረሰ በኋላ ዉጤቱን ማወቅ ሚቺለዉ፡፡

6 #ጥያቄ     ፦የጥያቄ ብዛት ምን ያህል ነው?

- #መልስ በ አጭሩ ለማስረዳት  በአንድ ዲፓርትመንት 17 ኮርስ ለመዉጫ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ እነኚህ 17ቱ ኮርሶች ለ 5 ግሩፕ ተከፍለው ነው  ፈተናዉ ሚወጣው። ለ አንድ ግሩፕ 100 ጥያቄ ማለት ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ለ 5 ግሩፕ ከ 500 ይሆናል ማሌትነዉ፡፡
( የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት )