Get Mystery Box with random crypto!

መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን ያስጠለሉ እና ቤት ያከራዩ የኦሮሞ ተወላጆች 15 ሺህ ብር ቅጣ | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን ያስጠለሉ እና ቤት ያከራዩ የኦሮሞ ተወላጆች 15 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለባቸው

በሸገር ከተማ የለገጣፎ ለገዳዲ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች በማስጠለላቸውና ቤት በማከራየታቸው የ15ሺ ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው ተናግረዋል።

በቅርቡ በተመሰረተው እና ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው በተባለው ሸገር ከተማ  ስር በተካተቱ ሰበታ፣ቡራዩ፣ለገጣፎ ለገዳዲ፣ሱሉልታ እና ገላን በተባሉ አከባቢዎች የአማራ ተወላጆች መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶባቸው ጎዳና ወድቀዋል።

ከሰሞኑ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ በኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች በሚታጀብ ግብረ ኃይል መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን በማስጠለላቸው እና ቤት በማከራየታቸው የ15 ሺ ብር ቅጣት በከተማ አስተዳደሩ እንደተጣለባቸው ነው የኦሮሞ ተወላጆች የተናገሩት።

የከተማ አስተዳደሩ የጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት ተገደው መክፈላቸውን የገለፁት የኦሮሞ ተወላጆቹ ያከራዩዋቸውን ሰዎችም ከቤታቸው እንዲያስወጡ መደረጋቸውንም ተናግረዋል።

ከአማራ ድምፅ ሚድያ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት በለገጣፎ ለገዳዲ ኗሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች፡ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን ጎዳና ላይ እንዳይወድቁ በሚል ወደ ቤታችን በማስገባት ማስጠለላችን እንዴት ወንጀል ይሆናል ያሉ ሲሆን፣ ይህ የኦሮሞን ህዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ለመለያየት የተሸረበ ሴራ ነው ብለዋል።

የኦሮሞን ህዝብ የጠቀሙ በመምሰል ለዘመናት በአንድነት የዘለቁ ወገኖቻችን ጋር እየለያዩን ነው ያሉን የኦሮሞ ተወላጆቹ፡ የአስተዳደር አካላቱ ከዚህ አይነት ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ቤት እንዳይከራዩ ጭምር ታግደው ጎዳና ላይ የወደቁ ሲሆን፣ አንድ አከባቢ ተሰባስበው እንዳይታዩ በፀጥታ ኃይሎች እንዲበተኑ ተደርገዋል።