Get Mystery Box with random crypto!

ትግራይ ትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክር | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

ትግራይ

ትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ በሰሜኑ ጦርነት "ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት" እንደገና እንዲቀጥል ያቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ ማድረጋቸውን የትግራይ ክልል ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሲኖዶሱን ጥሪ በጋራ በሰጡት መግለጫ ውድቅ ያደረጉት፣ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ የምሥራቃዊ ትግራይ፣ የማዕከላዊ ትግራይ እና የመቀሌ አሕጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የሲኖዶሱ ጥሪ ከዓመት በፊት ያቋቋምነውን "መንበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ጠቅላይ ቤተክህነት" ያገለለና ለጳጳሳት በግላቸው የተላከ መሆኑን ጠቅሰው ጥሪውን ተቃውመውታል ተብሏል። ሲኖዶሱ በበኩሉ፣ የትግራይ ጳጳሳት ውሳኔ በደብዳቤ ሲደርሰኝ ምላሽ እሰጣለሁ ማለቱን ዘገባው አመልክቷል።
(ዋዜማ ሬዲዬ)