Get Mystery Box with random crypto!

በደሴ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ ሐምሌ 5፣ 2014 (ማክሰኞ) በደሴ ከተማ | Ewunet Media(እውነት)

በደሴ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

ሐምሌ 5፣ 2014 (ማክሰኞ)

በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን÷ ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

እስከ አሁን የሞተ ሰው እንደሌለ ጣቢያችን ያረጋገጠ ሲሆን፥ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ፖሊስ መረጃ እሰጣለሁ ብሏል፡፡

በከድር መሀመድ
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta