አንድ የስራ ተቆጣጣሪ ባለሞያ የኮለን ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ፎርምወርክ ስራው ላይ መሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚገባው መሰረታዊ ነጥቦች [Elements of good Column formwork finish] 1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/ የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል። 2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/ ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ሌላ አስፈላጊ ስራ ነው። 3.አቀባዊ ሊኛ/Vertical alignment/ የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ አለበት። 4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/ የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው ሆኖ መቀመጡን ማረጋገጥ አለበት። 5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/ በዲዛይኑ መሰረት የኮለኑን ወርድና ስፋት ከፎርምወርኩ አቀናንሶ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ። 6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/ ከታወቀ መነሻ በመነሳት አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ። 7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/ ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። 8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት /Concrete cover/ ለኮንክሪት ሽፋን ዲዛይኑ የሚጠይቀው ተገቢ መጠን፣ በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው። https://t.me/ethioengineers1 2.5K viewsENG Sintayehu Melese, 09:11