Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ - ራማዳ ሆቴል አካባቢ ግንባታ እንዳይካሄድ ታገደ ቅንጡ ሠፈሮችን እያመሱ የሚገኙ ግንባታዎ | Ethio Construction

ቦሌ - ራማዳ ሆቴል አካባቢ ግንባታ እንዳይካሄድ ታገደ

ቅንጡ ሠፈሮችን እያመሱ የሚገኙ ግንባታዎች ጉዳይ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ ወጥ የሆነ ደረጃ አስኪዘጋጅ ድረስ በተለይ በአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ) ራማዳ ሆቴል አካባቢ የሚካሄዱ ግንባታዎች እንዲቆሙ ዕግድ አወጣ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ትናንት ሃምሌ 12 ቀን 2015 ዓም ለቦሌ ክፍለ ከተማ በፃፈው ደብዳቤ - በወረዳ 3 በተለይም ከራማዳ ሆቴል ግራ እና ቀኝ ውስጥ ለውስጥ የተካሄዱ ግንባታዎችም ሆኑ ግንባታ ፈቃድ የወጣባቸው ፕሮጀክቶች እንዲቆሙ አዘዘ።

በነዚህ አካባቢዎች በርካታ ባለስልጣናት ፣ ባለሃብቶች እና ዲፕሎማቶች የሚኖሩበት አካባቢ ቢሆንም - ግለሰባዊ ነፃነትን የሚጋፉ ህንፃዎች በብዛት እየበቀሉ በመሆኑ ቅድሚያ ተሰጥቶት መታገዱን የወዝ ኒውስ መረጃዎች አመልክተዋል ።

ይህንን እውነታ ከግምት በማስገባት የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ስጦታው አካለ (ኢንጂነር ) ለክፍለ ከተማው ጥብቅ ትዕዛዝ በሰጡበት ደብዳቤ ፣ አካባቢው በነባሩ ፕላንና አሰፋፈር ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች የሉበት በመሆኑ ፣ በድጋሚ እስኪጠና ድረስ ከ ሃምሌ 12 ጀምሮ ምንም አይነት ግንባታ እንዳይፈቀድ ፣ የተፈቀዱ ግንባታዎችም ለጊዜው ቆመው በቀጣይ እንዲሻሻሉ መወሰኑን አመልክተዋል።

ቀደም ሲል ዘመናዊ መኖሪያ የተገነባባቸው ሠፈሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ እና ትላልቅ ህንፃዎች እየተገነቡባቸው ነው። ግንባታዎቹ የተለመደ አኗኗርን እያወኩ ነባር ነዋሪዎችን እያስለቀቁ ከመሆኑም ባሻገር ፣ የመኖሪያ ሠፈሮችን እያሳጣ የሚገኝ ያልተገራ አካሄድ በመሆኑ ቅሬታ ሲቀርበብት ቆይቷል ።


https://t.me/ethioengineers1