Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቲ ቢሙ ካስት ሲደረግ በዋነኝነት የቢሙን ሎድ የሚሸከም በአራት አጠናዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ‹ | Ethio Construction

ክርስቲ

ቢሙ ካስት ሲደረግ በዋነኝነት የቢሙን ሎድ የሚሸከም በአራት አጠናዎች የተዋቀረ
ነው፡፡ ‹ ዋ › ፊደልን ይመስላል፡፡

ቢም ካስት ከማድረጋችን በፊት የምንከተላቸውን እስቴፖች ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

1. በመጀመሪያ ጎማ ውሃ ልክ አዙረን ቢሙ የሚያርፍበትን ቦታ
already ካስት የተደረጉ ኮለኖች ላይ ምልክት እናደርጋለን፡፡

2. በኮለኖች መሃል ምልክት የተደረገባቸውን ቦታዎች በሲባጎ እናገናኛለን - ሲባጎው የሚያርፍበት ቦታ የቢሙ ስር ወይም ቂጥ
ነው

3. በሁለት ኮለኖች መሃል - ኮለኖቹ ጥግ ላይ ሁለት ክርስቲ አቁመን ወገባቸውን እናሲዛለን

4. በሁለት ኮለኖች መሃል የሚያስፈልገውን ያህል ክርስቲ እንደረድርና በዳርኞቹ ክርስቲዎች ውስጥ ሁለት ማገሮች እናስገባለን፡፡ በመቀጠልም መሃል ላይ ያሉትን ወይም ወገባቸውን ያልያዙትን ክርስቲዎች ከማገሩ ውጪ በማድረግ ወገባቸውን
በሚስማር እናሲዛለን

5. ክርስቲዎቹ አናት ላይ በሁለቱም በኩል ማገር እንመታለን

6. ሌላ ትይዩ ቢም ካለ ከእስቴፕ 1-5 ያለውን እንሰራለትና ከዚኛው የክርስቲ ግሩፖች ጋር በማገር እናያይዛቸዋለን

7. በተወሰነ ርቀት ላይ ስላቡ የሚያርፍበትን ቋሚዎች እናቆማለን

8. ለውሃ ልክ የዘረጋነው ሲባጎና የክርስቲው አናት ልክ ከመጣልን እንደዛው እንተወዋለን - ልክ ካልመጣ ግን ‹ ኩኞ › በክርስቲውና
በሲባጎው (ፎንዶው ስር) መሃል እናስገባለን

9. ፎንዶውን የቢሙን alignment ጠብቀን እናስቀምጣለን

10. ስፖንዳ እንመታለን - እስፖንዳውን በአጠና እንደግፈዋለን

11. የቢሙን reinforcement አስገብተን ቢሙን ካስት እናደርጋለን


-ኩኞ -ቁርጥራጭ አጠና
-ፎንዶ - ቀጥታ ከቢሙ ስር የሚያርፍ ተሸካሚ ፎርም ዎርክ
-እስፖንዳ - ቢሙን ከጎን የሚይዝልን ፎርም ዎርክ


https://t.me/ethioengineers1