Get Mystery Box with random crypto!

92 ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ በዛሬዉ እለት 92 ኢትዮጵያውያን ከየመን | HabeshaNet.

92 ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በዛሬዉ እለት 92 ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀን የተውጣጣ የልዑካን ቡድን ወደ ኤደን በመሄድ የሊሴ ፓሴ የመስጠት ስራ አከናውኗል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተዉ ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሀገራቸዉ እንዲመለሱ የተደረገዉ ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመተባበር ነዉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል እንዳደረጉላቸዉም ተገልጿል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም