Get Mystery Box with random crypto!

ማሊ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ታገደች የአፍሪካ ህብረት የፀጥታና ሰላም ኮሚሽን በትናንትናው ዕ | HabeshaNet.

ማሊ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ታገደች የአፍሪካ ህብረት የፀጥታና ሰላም ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት በመፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚዳንቷን ከስልጣን ያስወገደችውን ማሊን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት አግዷታል።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አገሪቷ ህገ መንግሥታዊ ስርአት እስክታሰፍን ድረስና በቁጥጥር ስር ያሉትን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች ባለስልጣኖች እስኪለቀቁ ድረስም እግዱ ይቆያል ብሏል።

የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሲሪል ራማፎሳም በወታደራዊ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ያሉትን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታም እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

ሊቀ መንበሩ ሲሪል ራማፎሳ አገሪቷ በአስቸኳይ ወደ ሲቪል አስተዳዳር እንድትመለስም አሳስበዋል።

የአውሮፓ ህብረትም ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር እንዲለቀቁ መጠየቁን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል። https://www.facebook.com/ETHIOID/photos/a.2880951031917937/3553278421351858/?__cft__[0]=AZWAKlSX5jwem09nad9NWp3vKc-2DZDa7dzkbPLzmAuM7BvAPZH0auie-DlsnRy2nC49NaSVFCpqvdsQQR-Cc_DHA-jAbpVkqppJykqvha7X-YAMrmyHUht_gHTyEWi5x2i5ZZPsexyv45jq3fBHSlvp&__tn__=EH-R