Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1038 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው | HabeshaNet.

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1038 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው።

ተጨማሪ 232 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 17ሺህ 323 የላቦራቶሪ ምርመራ 1038 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 27 ሺህ 242 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 232 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 660 ሆኗል።

ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 492 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 195 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 15 ሺህ 088 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 567 ሺህ 442 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

HabeshaNet.
We will provide Coronavirus updates about Ethiopia and the globe!

ይደግፉን | ያስተዋውቁን!

For any questions contact us http://t.me/EthioCoronavirusInfobot

https://www.youtube.com/c/TheNewEthiopiaTube?sub_confirmation=1
https://t.me/ethiocoronainfo