Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ | Ethio Anti Corona

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ወንድ እና 56 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ3 እስከ 72 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 147 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሶስቱ (3) የውጭ ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 123 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 13 ሰዎች ከአማራ ክልል እና 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 250 ደርሰዋል።