Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_university_info — ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_university_info — ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_university_info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.06K
የሰርጥ መግለጫ

🛂 ይህ ቻናል የግቢ ተማሪዎችን ችግር እግር በእግር እየተከታተለ ለሚማለከተዉ አካል ያሳዉቃል መፍትሔ እንድያገኝም ጥረት ያደርጋል።
👉ለስራችን ጥራት የእናንተ ከጎናችን መሆን ትልቅ ዋጋ አለዉ።
ይህ ቻናል
የናንተዉ
ለናንተዉ
ከናንተዉ
የሆነ ቻናል ነዉ።
👉 እባካችሁ አስተያየት/Comment ካላቹ
እዚህ ላይ ፃፉልን
@think_positiive
💙💛ከልብ እናመሰግናለን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 11:41:49 ጥንቃቄ ለ ወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች

የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ከግቢው ጋር መወያየት እና መፍትሄ መምጣት አለባችሁ።

ሆን ብለው ተማሪዎችን እና ማሕበረሰቡን ለማሸበር የተላኩ ግብረ አበሮች ስላሉ በሰማችሁት ነገር ሁሉ መረበሽ የለባችሁም።

በድጋሚ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወልዲያ አከባቢ ላይ መሆኑን መረጃዎች እየተሰራጩ ናቸው።

ከተለያዩ ሰዎች መረጃ ተቀብለን ነበር ....አንዳንዱ #ወልዲያ ተይዛለች ይላል...አንዳንዱ አልተያዘችም ይላል። ይህ የሚያሳየው በህዝቡ መሃል የውሸት ዜናዎች እየተሰራጩ መሆኑን ነው።

ስለዚህ የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አትረበሹ, መደናገጥ አያስፈልግም። ተረጋጉ

ሌላው ነገር የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሁሉም ነገር ዝግጁ ሆናችሁ መጠበቅ እና እውነት የሆኑ መረጃዎችን ብቻ መከታተል ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
557 views Muhaba Mass , 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 01:49:26 #ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

ኢፕድ/ቲክቫህ
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
1.2K views Muhaba Mass , 22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 01:49:25 ‹‹የመውጫ ፈተና በትምህርት ጥራት ያለውን ችግር አንዱ የመፍቻ አማራጭ እንጂ ብቸኛ ርምጃ አይደለም›› – ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ

የዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ከሚወሰዱ ስትራቴጂያዊ ርምጃዎች ውስጥ አንዱ እንጂ ብቸኛና የመጨረሻ ርምጃ አለመሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ገለጹ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እንደሚተገበር በሚጠበቀው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ማስጠበቂያ የመጨረሻና ብቸኛው ርምጃ አይደለም፡፡ ብቁ የሰው ሃይል በማዘጋጀት ወደ ኢኮኖሚ መግባቱን ማረጋገጫው አንደኛው መንገድ እንጂ ብቻውን የትምህርት ጥራት ሊያመጣ አይችልም፡፡

የመውጫ ፈተናው ተመራቂዎች በተማሩበት ሙያ፤ ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ገንብተው ስለመውጣታቸው የሚመዝን መሆኑንም ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፡፡

ባለዲግሪ ዋጋው አይታወቅም፡፡ ገበያው የሚለይበት አካሄድ የለውም፡፡ ዲግሪ በያዙ ተመራቂዎች መካከል በብቃት የሙያውን ምሉዕነት ተላብሶ የተመረቀው የትኛው እንደሆነ መመዘኛው የሚያረጋግጥ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

‹‹ሁሉም ዲግሪ አንድ አይነት ሆኖ አይታሰብም፡፡ ራሱ ለሚማረውም፣ የቤት ስራ እየተሰራለት የሚመረቀውም ባለዲግሪ ነው፡፡ ለሁሉም እኩል ዋጋ ሰጥቶ ወደ ገበያው መቀላቀል ተገቢ አይደለም›› ሲሉ ዶክተር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡ በተለመደው አሰራር ቢቀጥል ከትምህርት ጥራት በላይ በኢኮኖሚው ኢ-ፍትሃዊነት እንዲነግስ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

ምዘናው የሚሰጠው በመጀመሪያ ዲግሪ ላይ ብቻ መሆኑን፣ ትግበራው አገራዊ ፖሊሲ እንደመሆኑ በግል፣ በመንግስትም በየትኛውም ተቋም የሚማር ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ካለፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበትና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ዴኤታው፤ ለምዘናው የመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁትን በዓመት ከ150 እስከ 180 ሺ ማስተናገድ የሚችል አቅም መኖሩን ተናግረዋል፡፡

የሙያ ማሕበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፣ የመውጫ ፈተና ስራን ከመንግስት ላይ እንደሚወስዱም ነው የጠቆሙት፡፡

ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመው፤ ትምህርቶቹን የሚያዘጋጁ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ስራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ ብለዋል፡፡

መምህራንን በተለያዩ አማራጮች የትምህርት ደረጃቸውንና የመመራመር አቅማቸውን እንዲያሳድጉና የተለያዩ የማስተማር ሥነ ዘዴዎችንና ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡

ተማሪዎቹ ብቁ ሆነው መውጣታቸውን ግብ አድርገው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮና በትኩረት እንዲለዩ ተደርጓል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪ ቆይታ ዘመን ወደ አራት ዓመታት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ ሂደቱ ተማሪዎቹ የከፍተኛ ትምህርት አውድን ተገንዝበው የሚፈልጉትን፣ መክሊታቸውንና አቅማቸውን ለይተው ማሳካት የሚችሉትን የትምህርት መርሃ ግብር መርጠው እንዲገቡ እንደሚያስችላቸውም አብራርተዋል፡፡

ተማሪዎች ሲገቡ እንጂ ለምን ወውጫ ላይ ይፈተናሉ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢሆንም ወደ ዩኒቨርሲቲ እያስገባን ያለነው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈትነው መሆኑን መዘንጋት እንደማይገባ ገልጸው፤የመውጫ ፈተናውም ቢሆን፤ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ ብቁ ሆኗል የሚለውን እንደማይገልጽም ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2011 የመውጫ ፈተና ሊሰጥ እንደሚችል በግልጽ አስቀምጧል፡፡ የሪፎም አካል ነው፣ የሪፎም አጀንዳን መንግስት የሚመራው እንደመሆኑ ሂደቱን ትምህርት ሚኒስቴር መንግስትን ወክሎ መስራቱ የስልጣን ሽሚያም፣ መጣረስም እንደሌለውም አመልክተዋል፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
1.9K views Muhaba Mass , 22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 15:32:38
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በቡሬ ካምፓሱ ያሰለጠናቸውን 663 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛ፣ በማታ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

የቡሬ ካምፓስ 7ኛ ዙር ሰልጣኞቹን ያስመረቀ ሲሆን ከዛሬ ተመራቂዎች መካከል 197ቱ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች ትላንት ማስመረቁ ይታወቃል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
1.1K views Muhaba Mass , 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 15:32:33
በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ ትምህርት ጉድለቶች እንደነበሩበት በጥናት መለየቱን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ተሻለ ብሬቻ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በመሆኑም ጉድለቶቹን የሚሞላና ሰልጣኞች በሁሉም ሙያ የተሟላ እውቀትና ክህሎት ይዘው እንዲወጡ የሚያደርግ አዲስ ሥርዓት ትምህርት በመጪው ዓመት ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

ሥርዓተ ትምህርቱ የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈውበት የተዘጋጀ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ለኢፕድ ተናግረዋል።

"ሥርዓተ ትምህርቱ ሠልጣኞች ኮሌጆች ውስጥ እያሉ እንዴት ሥራ መፍጠር እና ራሳቸውን ለሥራ ማዘጋጀት እንደሚችሉ በተግባር የሚለማመዱበትን ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን" ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ከ1 ሺህ 800 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ይገኛሉ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
810 views Muhaba Mass , 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 16:32:16
ከ10 ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የምረቃ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ በሚገኙ 14 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ትምህርታቸውን የተከታተሉ 10 ሺህ 120 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የምረቃ ስነ-ስርዓት በሚሌኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

ተመራቂዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር በሚገኙ 6 የፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች እና 8 ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5 የተለያዩ ስልጠናዎች መውሰዳቸው የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
711 views Muhaba Mass , 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 16:32:15
#SPHMMC

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዛሬ 75 ዓመት ነበር የተመሰረተው።

አሁን ላይ አውቶቡስ ተራ በሚባለው አካባቢ ሐምሌ 16/1939 ዓ.ም ምስረታውን ያደረገው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፤ አሁን ወዳለበት ጉለሌ አካባቢ የተዘዋወረው በ1961 ዓ.ም ነበር።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት መልካም አሻራውን በማሳረፍ እዚህ ደርሷል።

ኮሌጁ ወደፊት የሕክምና ዩኒቨርሲቲ ለመሆን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
576 views Muhaba Mass , 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 15:20:44
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎቹን የተማሪዎች ቤተሰብና እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ፥ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛ፥ በተከታታይና በክረምት መርሐ ግብር ወንድ፥ 1416 ሴት፥ 796 በአጠቃላይ 2212 ተማሪዎችን የዕለቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር በላይ ካሣ በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት እያስመረቀ ይገኛል፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
586 views Muhaba Mass , 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 08:21:03
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የነባር እና አዲስ ገቢ የ2014 ዓ.ም #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 20 እስከ 22/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ጥሪው ለመጀመሪያ ዲግሪ፣ ለሁለተኛ ዲግሪ እና ለPHDT የክረምት ተማሪዎች የተደረገ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
787 views Muhaba Mass , 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 08:21:03
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁሉም ነባር #የክረምት እና #የእረፍት ቀናት መርሃ ግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15 እስከ 18/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተመሳሳይ ፈተና ያለፉ አዲስ ገቢ #የሁለተኛ ዲግሪ #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ 18/2014 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል የተባለ ሲሆን ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
645 views Muhaba Mass , 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ