Get Mystery Box with random crypto!

ለ6ኛ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ጀምራል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ለ6ኛ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ጀምራል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች በጋራ የተዘጋጀ ሞዴል ፈተና በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የ6ኛ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሰጠት ጀምራል፡፡

ሞዴል ፈተናው ከሰኔ 7-9 /2015 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የፈተና አስተዳደርና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተማሪዎች በሞዴል መልስ መስጫው ላይ በቂ ልምምድ እንዲያደርጉ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዘንድሮው ከተማ አቀፍ ሞዴል ፈተና በ8ኛ ክፍል 75̡100 ተማሪዎች በ766 ት/ቤቶች እንዲሁም በ6ኛ ክፍል 75̡090 ተማሪዎች በ788 ትምህርት ቤቶች በመደበኛ በማታና በግል እንዲሁም 53 535 የሚሆኑ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተናውን የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy