Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ፡፡ -ትምህርት ሚኒስቴር | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ፡፡ -ትምህርት ሚኒስቴር

በሰሜኑ ጦርነቱ ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው መስከረም ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በክልሉ የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት የምግብ፣ የመኝታ እና የህክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ራያ ዩኒቨርሲቲ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማሟላት ትላንት ሰኔ 06/2015 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

መቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ወራት ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር እንደሚጨርሱና ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው፤ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ እንደሚችል ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ መሰረታዊ ነገሮችን አሟልተው በመጪው መስከረም ሥራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ብለዋል። #ኢፕድ
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy